Sewoch be betekrstiyan tarik yetedergu 3tu gubaye zerezer mereja kale esti lakulegn le orthodox teketayoch
Feb 24, 20223 ጉባኤያት ናቸው። 1ዱ ጉባኤ ኒቂያ ነው። አርዮስን ለማውገዝ 318 ሊቃውንት በ325 ዓ.ም የተደረገ ጉባኤ ነው። በዋነኝነት አርዮስን ለማውገዝ ይሁን እንጂ በዚሁ ጉባኤ ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ የሆኑ ሥርአቶች ተሰርተዋል ለምሳሌ #በቤተክርስቲያን ዋዛ ፈዛዛ ነገሮች መጫወት እንደማይገባ #አዲስ አማኝ የሆነን ሰው ፈጥኖ መሾም እንደማይገባ ለአብነት መጥቀስ ይቻላል። 2ተኛው ጉባኤ ቁስጥንጥንያ ነው። የዚህ ጉባኤ ምክንያት የመቅዶንዮስ እና የአውሳብዮስ ክህደት ነው በ381 ዓ.ም በትልቁ ቴዎዶስዮስ ዘመን ነው። በዚህም ጉባኤ ከተወሰኑ ተጨማሪ ሥርአቶች ውስጥ # ኤጲስ ቆጶሳት ከሀገረ ስብከታቸው ውጪ በሆነ ጉዳይ መግባት እንደሌለባቸው። # ሃይማኖትን በተመለከተ በሃይማኖት አባቶች መዳኘት እንደሚገባ። ማንሳት ይቻላል። 3ተኛው ጉባኤ ኤፌሶን ነው። ይህ ጉባኤ በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን በቅዱስ ቄርሎስ መሪነት በ401 ዓ.ም ንስጥሮስን ለማውገዝ የተዘረጋ ጉባኤ ነው። በዚህ ጉባኤ ላይ ከተወሰኑት ውሳኔዎች ውስጥ #ከመናፍቃን ጋር የሚተባበር ካህን(አባት) ከሥልጣ ጡ መሻር አለበት። #የንስጥሮስን ትምህርት የሚያራምድ ምዕመን መወገዝ እንዳለበት ተደንግጓል። ከብዙ በጥቂቱ ይህ ነው። የማትቀበለው ጉባኤያት አሉ ለምሳሌ ጉባኤ ኬልቄዶን (ጉባኤ ከለባት/አብዳን ) ይሰኛል በንግስት ብርክልያ ዘመን የተዘረጋና ጉባኤና ለዲዮስቆሮስ መሰደድ ፂም መነጨት ጥርስ መውለቅ ምክንያት የሆነች የምንፍቅና ጉባኤ ነው።
Feb 25, 2022