ሰላም ውዶች እንዴት ናችሁ ያስጨነቀኝ ነገር አለ እና በጣም ተጨንቄአለሁ እንኪ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ሀሳባችሁን አካፍሉኝ በፍጥነት አክሙኝ ታሪኩ እንዲህ ነው የአንደኛ አመት የግቢ ተማሪነኝ እሷም ከኔጋ አንድ ግቢ ናት እና ከሷጋ ቀን በቀን መገናኘት እና ማውራት ጀመርን እኔም ሳላስበው አፈቀርኳት እና ለሷ ያለኝ ስሜት ቀን በቀን ጨመረብኝ እሷም ስትስቅ ስትጫወት ሳያት የወደደችኝ መስሎኝ ነበር ግቢው በሙሉ ስለኛ ግንኙነት ነው ሚያዎሩት በቃ ምን ልበላችሁ ጦፏል ከዛ የሆነ ቀን ለኔ ያላትን ስሜት ጠየኳት የኔንም ስሜት ነገርኳት እንደምወዳት እንደማፈቅራት የሷ ምላሽ ግን እንደጠበኩት አይደለም ምንም ስሜት የለኝም አንተን በሌላ መንገድ አስቤክ አላቅም አለችኝ አብረሽኝ የነበርሽው እየቀለድሽብኝ ነበር ስላት አዚህ ግቢ እንዳንተ የቀረብኩት የለም እወድሃለሁ ግን ፍቅር ውስጥ ለመግባት አላሰብኩም ትለኛለች ከዛ ስርቃት ትቀርበኛለች እኔ ደግሞ ናፍቆቷ ጨመረብኝ አለማሰብ ለመጀመር ሳስብ ይበልጥ ትናፍቀኛለች በጣም ተቸገርኩ እርዱኝ እባካችሁ
Feb 19, 2022Mnabat fetnhbat lhon ychlal bro eski zm blh be guadgninetachu qetlu
Feb 19, 2022