selam ye nuro wdnetu endi eyasasake eko hede lelaw africa hager 10 birr chemere bilo miyaregewn eyayen egnaw besint chgroch tekeben beza lay nurow eyehede mefthe mndnew bilachu tasbalachu eski kuch bilachu yezare 10 amet asbut mn aynet gize yimetal bilachu tasbalachu plus yahunu nuro wdnet hizbu endet new mastekakel michilew mengst endehone tegntual bizu negeroch lay balaye eyalefe new ena eski hasabachun situbet silasasebegn new bezi keketele minserawna mininorew mn lihon new😏
Feb 18, 2022አይ ፓምፕ አሁንማ አያሳስብህ ወደድንም ጠላንም መፍትሄው ቀርቧል። ባይሆን ቆት ካለች አንዲት ጽሁፌ ልጋብዝህ። ባትጠቅምም አትጎዳም። #ረዘም ትላለች # ትዕግሥት አንብቧት ተጋበዙልኝ። የኑሮ መወደድን Definition የተረዳውት ልጅ እያለው ነበር። በ5 ሳንቲም 5ጠጠር ከረሜላ መግዛት ለ90ዎቹ ልጆች የተለመደ ነበር። የዛ ትውልድ አካል በመሆኔ እንደማንኛውም የ90ዎቹ የኢትዮጵያ ልጅ በ5ሳንቲም 5ጠጠር ገዝቼ መኮርሸም አንጀቴን ነበር የሚያርሰው።በድንገት ግን ኑሮ ተወደደ።ስለ ኑሮ መወደድ ጭምጭምታ ብሰማም አልተረዳውትም ነበር እንድረዳው እስካደረገኝ አንድ ክስተት ድረስ። ነገሩ 5ሳንቲም ተቀብዬ ጀማል ሱቅ ስደርስ ነበር መረዳቴ የጀመረው። የጀማል ፊት ከወትሮ በተለየ መልኩ በግርምት ሳቅ ተሞልቶ ነበር። የኔን ፊት እስኪያይ ማለቴ ነው። ቀረብ ብዬ ጠጠር ከረሜላ ስጠኝ በማለት 5ሳንቲሜን መዥረጥ አድርጌ ስሰጠው ጀማልም የጠጠር ከረሜላውን ማስቀመጫ እቃ ወጣ አድርጎ ቆጠር ቆጠር አድርጎ 3ጠጠር ሰጠኝ። አልሄድኩም። 2ጠጠር ከረሜላ ጀማል ጋር ስለሚቀረኝ። እጄን አላጠፍኩም ቀሪውን ቆጥሮ እስኪያስረክበኝ። ጀማል ይሄኔ አለመሄዴን ተመልክቶ መወደዱን ሊያስረዳኝ ሚኪ የ5ሳንቲም 3ሆኗል አለኝ። ወሽመጤ ተቆረጠ። ቅንድቤን ወደታች አይኔን ወደላይ ክንፈሬን ከጥርሴ ውስጥ መሸጎር ከመቅጽበት የጀማልን የቀድሞውን የግርምት ፈገግታ ወደ ትካዜ እንድለውጠው ያደረገ ገጽታ ነበር። ለወትሮ 5ተቀብዬ 2ቱን በአንድ ግዜ አፌ ውስጥ መክተት የተለመደ ተግባሬ ቢሆንም ሲወደድ ግን አላደረጉትም። እንደሰጠኝ ጭብጥ አድርጌ እቤቴ ድረስ መሄድ ብቻ ነበር የታየኝ። ገባው ከቤቴ። የእጄ ሙቀት የከረሜላውን ከለር አድምቆታል። ተጽናናው😄 መቆጠብ አለብኝ አልኩ ለራሴ። ጠዋት አንድ ማታ አንድ ፍሬ መድኃኒት እንደታዘዘለት ታካሚ አንድ አንዷን በቀን 3ቴ ወሰድኳት። ከዛን ወዲ የኑሮ መወደድን ስሰማ እሳቀቃለው።እግዚአብሔር ይመስገን ተላመድን አሁንማ። በተለይ ከቅርብ ግዜ ወዲኽ መከራከርም እንዳንችል ሆነን የጠዋቱ ለከሰዓት እየጨመረ "ጨመረን" አላምደውናል። ተመስገን። በየሚዲያው የሚቀርቡ የሴት ተዋናዮችን እድሜ ባንሰማ በምን እንጽናና ነበር? የሆነ ሆኖ ቸርነቱን ከኛ ያላራቀ አምላክ የእለት ጉርስ አነሰም በዛማ ጣፈጠም መረረም አላሳጣንም። አደባባይ የወጣ ርሀብ እየሰማን እንደሆነ ሁሉ አደባባይ ያልወጣ በየቤቱ የተራበ ወገን አለን እና እግዚአብሔር በቸርነቱ እንዲመግባቸው በጸሎት ከመለመን ባሻገር ካለን ከፍለን ማጉረስ ቀደን ማልበስን መልመድ ይኖርብናል። አንዳንዶች የገንዘቡ ምንጭ ከወዴት ነው በሚያስብል መልኩ አይናቸው አሽተው ስጋ ቤት በመገኘት ጥሬ ከብስል ሲያማርጡ የነጋበት ጅብ እንኳን በአግራሞት እጁን አፉ ላይ በመጫን "እንዴ ጅብ" ብሎ እንደሚያልፍ ከአንዳንድ ጅቦች ለመስማት ተችሏል። ብላ ጠጣ መብትኽ ነው። ግን በልክ። በቀን 3ግዜ መብላት እንደ ቅንጦት እየታየ ባለበት ሁኔታ ላይ እንዲ ስትሆን በራሱ ኃጢያት ነው። በባዶ ሆዱ ቫዝሊን ተቀብቶ ከወዛ ህብረተሰብ ጋር መኖርኽን አትዘንጋ። አየኽ ግዜ ያልፋል ችግርም ያልፋል። ችግሩ ባያልፍ እንኳን ባለችግሩ ያልፋል። ለሚያልፍ ግዜ እና ለሚያልፍ ችግር ዛሬ አንተ ስላለክ ብቻ ውድ ጫማ ውድ ልብስ ውድ ስልክ ውድ መኪና ይዘኽ ሌላው ሲቸገር ከንፈርክን ብቻ መጠክለት አትለፍ ፍላጎትክን ገድበክ ለተቸገሩት ድረስ። After all ሁላችንም አፈር ነን። የእንግሊዘኛዋ ነገር አንዱ ስቸገር ተመልክቶ መጽውቶኝ ነው።ምን ለማለት ፈልጌ ነው ቆርሰኽ የምታጎርሰው ቀደኽ የምታለብሰው ባይኖርክ እንኳን ጠጋ ብለኽ ወንድሜ ወገኔ በለው እንዲ ባለ ግዜ ላይ እንኳ ብሔር ጎሳ ነገድ አትበል። ወንድሜ ወገኔ የኑሮ ውድነት ግን በዚኽ ከቀጠለ ምን ይጠብቀናል ? ያዝልኝ እዚጋር።በዓል እየደረሰ አይደል በጣም ያሳሰበኝ ለ500ብር ዶሮ ማለቴ ጫጩት የ600 ብር ዘይት መገዛቱ ነው።😞 ቢሆንም ከብዙ ውጣ ውረድ በውኋላ አንድ መላ አበጅቻለው። ተጠቀምበት።ይኸውም አታክልት ቤት መግባት አታክልት ማዘዝ አታክልቱ ሲመጣ አብሮ ከሚቀርበው አቼቶ እና ዘይት የሚያስፈልግክ ዘይት እንደመሆኑ አስቀድመክ ብልቃጥ ይዘክ በመግባት በአታክልቱ ላይ ጥቂት ጠብ በማድረግ ቀሪውን ብልቃጥክ ውስጥ መገልበጥ እንደ ዋጋውማ ሳህኑንም ይዘክ መውጣት ነበረብክ ይሁን ወገን በወገኑ አይጨክንም ሳህኑን ተወው። ዘይቱ ላይ ብቻ ይሁን ትኩረትክ። በአግባቡ ጥርግ አድርገክ በልተክ ዘይቱን ይዘክ ልትወጣ ስትል ከቻልክ ታመልጣለክ ከተባነነብክ ግን ራስክን ለዱላ አዘጋጅ ። እንበል ተያዝክ ግብ ግብ ላይ ነክ የሚያሳዝነው የጠገበ ፖሊስ ይመጣ ከመሰለክ ነው። ልብሱን ያሳመረ የተራበ ፖሊስ ጸቡን ለማብረድ በሚል አንተን ሌባ በማለት ባለ አትክልት ቤቱን ሌባ እንዴት ይመታል ተይዞ ለፍርድ ይቀርባል እንጂ በማለት ሁለታችሁንም ድባቅ እየመታ እስኪጣራ ዘይቱ እሱ ጋር መቅረቱ ነው። ስለዚህ በተራበ ፖሊስ ተደብድበክ እንዳሰብከውም ሳትበላ ከምትቀር መጀመሪያውኑ ባለ አትክልት ቤቱና አንተ ያላችሁ አማራጭ መስማማት ብቻ ይሆናል ማለት ነው። መካፈል። መግባባት+መስማማት=መብላት አለመግባባት+አለመስማማት=መበላት ምርጫው ያንተ ነው። እንዳንባላና እንዳን'በላ ተስማምተን እንብላ:: ልልክ ነው። ሚኮጵያ ነኝ።
Feb 19, 2022