ለተፈላሳዊዎች! “ሁሉም ነገር በምክንያት'ና ውጤት የተገኘ ነው፤” ትላላችሁ! ሀሳባችሁ እውነት ቢመስልም አንዳንድ ነገሮች ግን ያለ ምክንያት ውጤት የሆኑት እንዴት ነው!? ለምሳሌ፥ ጨለማ በምን ምክንያት ውጤት ሆነ? ዘላለማዊነትስ? የኳንተም ፊዚክስ ቲዮሪው የሁሉም አስገኝ ነው የሚባለውስ ኢነርጅስ? እግዜር የሚሉት ነገር ካለስ እንዴት ያለምክንያት ውጤት ሆነ? ቁስ አልባው ህዋስ (ማለቴ አለም ሳትፈጠር በውስጡ ጋላክሲዎች፣ ፕላኔቶች፣ አስትሮይዶች… ወዘተ ያላቀፈው) በምን ምክንያት ውጤት ሆነ? …ፍፁም ፀጥታስ በምን ምክንያት ውጤት ፀጥ አለ?
Feb 17, 2022ጥሩ ነው። አንተ ገና ፈጣሪ አለ የለም ላይ ልትሆን ትችላለክ እኛ ደግሞ የፈጠረን እግዚአብሔር አለ ብለን እስካመንን ድረስ እግዚአብሔራችንን ልታከብር ይገባል በቅድሚያ። እግዜር የሚሉት #ነገር ካለስ። ላልከው አፍክን ጠብቅ። በቅድሚያ "ሁሉም ነገር"በምክንያት እና ውጤት የተገኘ ነው የሚለውን እንመልከት። ሁሉም ነገር በሁለት ነገር ይጠቃለላል ፈጣሪ በፍጥረቱ ሸማኔ በቁጤቱ እንዲል 1. ፈጣሪ :- አስገኚ ምንጭ ምክንያት 2 ፍጡር :- ዉጤት መገለጫ ዝርዝሩን ጥበብ እንዲሆንህ ለልቦናህ በመተው። ጥልቅ ትንታኔ ቢሻም በአጭሩ ሁሉም ውጤት ሊሆን የቻለው በሀሳብ ምክንያት ነው።
Feb 17, 2022