ሰላም ሰዎች ስሜ እንኳ ይለፋቹ ግን እኔ 17 አመቴ ነው መካከለኛ የሚባል ቁመት አለኝ ማለቴ ከእኩዮቼ አንፃር እና ወደገደለው ስገባ ኳስ ተጫዋች መሆን ፈልጋለው እና አሁን ልምምድ ስንሰራ የጫወታ ግዜ ላይ ኳስ አሪፍ ኮንትሮል አለኝ እና አሪፍ እጫወታለው ግን ኳስ ከተሰጠኝ አይኔ እሚያየው ኳስኳሱን ብቻ እና ልክ ኳስ እግሬስር ሲገባ እደነግጣለው መፍትሄ ካላቹ ጀባ በሉኝ እስቲ እባካቹ በትህግስት ስላነበባቹ አመሰግናለው።
Feb 16, 2022የብዙ ሰው ችግር ነው መፍትሔው ደሞ ማሰብ መጀመር ያለብህ ኳሳ እግር ስር ስትደርስ ሳይሆን ቦታ ስትይዝ ኳሷ ስትመጣ ምንድን ነው የማድርጋት ብለህ ነው። ይሄንን በማድረግ በትንሽ ልምምድ መለወጥ ትችላለህ። መልካም ልምምድ ! በትዕግስት መልሴን ስላነበንክ አመሰግናለሁ
Feb 17, 2022