ስለ Valentine's day ምን ታስባላችሁ እኔ ስለማይመቸኝ ከብዙ ሰዉ ጋር ስለምከራከርበት ነው
Feb 12, 2022እንደ እኔ አጠቃቀማችንን እናስተካክል እንጅ ይጥፋ ባይ አይደለሁም የፍቅረኛሞች ቀን እኮ መኖሩ ጥሩ ነው። መኖሩ ይሁን ግን ቀኑን በአሸሜ ገዳሜ እና በዝሙት ምናምን ሳይሆን በጥሩ ነገር አክብረነው ቢሆን ነው የምመረጠው ለምሳሌ የኔ ጓደኛ ከሚስቱ ጋር ባለፎ እየትዘናኑ እና መንፈሳቸውንም እያረኩ ነበር ያከበሩት ጠዋት ቀይ መስቀል ሄደው ደም ለገሱ ከስዓት ሲኒማ ገቡ ስጦታ ተሰጣጡ ምናምን ሲመሽ ቤቷ አስገብቷት ሄደ። አሁን እንዲህ ቢሆን ጥሩ ነው በዓሉ የምያስጠላው ዝሙት መጠጥ ገለመሌ ገለመሌ ሲገባበት ነው እንጅ እኔ Valantine Dayን በደፈናው አልጠላውም
Feb 12, 2022