#religion በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ ለሰው ልጅ በእንስሳት ላይ ስልጣን እንደተሰጠው ይናገራል፡፡ ምን ማለት ነው? እንኳን ትልልቅ አውሬዎችን ቀርቶ ውሻና ድመትን የሚፈራ የሰው ልጅ እንዴት ነው በእንስሳት ላይ ስልጣን የሚኖረው? እንደውም እነሱ በእኛ ላይ ስልጣን ያላቸው ይመስላል፡፡ምክንያቱም የመብላትም የማስፈራራትም አቅም አላቸው፡፡ እውነታው ይህ ከሆነ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ያለው ምን ማለቱ ነው? ስልጣን ካለንስ ምን ዓይነት ስልጣን ነው? እንዴት ነው የምንጠቀመው? ስልጣን እንዳለኝስ እንዴት ማረጋገጥ እችላለሁ?ሙስሊሞችም ሀሳብ ብትሰጡበት ደስ ይለኛል፡፡ አመሠግናለሁ፡፡
Feb 09, 2022i think ዘፍጥረት ላይ '... በምድር ባሉት ሁሉ አነገስኳችሁ... ምናምን ብሎ አዳምና ሄዋንን መርቋል መሰለኝ ! እና ከዬት እንደመጣ ባላቅም 'የእንሰሳትን ስም ያወጣው አዳም ነው' የሚባልም ተረክ አለ ፤ በአጠቃላይ ግን እንዳልከው የማንም አለቃም አዛዥም አንመስልም (የገዛ ቤቴ ለመግባት የማልፋቸው ውሾችና የመነከሱ ሰቀንን 😖 ደሞኮ ያጉረመርማሉ ከነሱም ብሶ) ብቻ እስካሁን ያወቅነው መሬትን ከነሱጋ እንደምንጋራ ነው 🤷🏾♂
Feb 09, 2022