Ye hawrayat tarikachewn yemtawku 1petros 2endriyas 3 Thomas 4mathiwos 5 smon 6filipos Ebakachu ahun lakulg
Feb 05, 2022የቤተክርስቲያን ታሪክ የሚል መጽሐፍ አለ፥ እሱ ላይ አንብብ። ከዛ በላይ ግን ገድለ ሐዋርያት አለ፥ ብዙም አይገኝም እንጂ። በትንሹ ለመግለጽ 1- ጴጥሮስ- የሐዋርያት አለቃ፣ የእንድርያስ ወንድም፣ አገልግሎቱ አውሮፓ፣ የአንጾክያ መንበር መስራችና ጳጳስ፣ የሮም መንበር መሥራች እና የመጀመርያ የሮም ጳጳስ፣ ዝቅዝቅ ተሰቅሎ ሰማእትነትን የተቀበለ። 2) እንድርያስ፣ አገልግሎቱ አውሮፓና ትንሹ እስያ(ቱርክ)፣ የመጀመርያ የቁስጥንጥንያ ሊቀጳጳስ፣ X ቅርጽ ባለው መስቀል ላይ በግሪክ ተሰቅሎ ሰማእትነትን የተቀበለ። 3)ቶማስ- አገልግሎቱ ህንድ፣ የድንግል ማርያምን ፍልሰተ ሥጋን ያየ ብቸኛ ሐዋርያ፣ የህንድ ማላንካራ ቤ/ክ መስራችና የመጀመሪያ ማርቶማ(ጳጳስ)፣ የሰውነት ቆዳውን ገፍፈው ጨው ከነሰነሱበት በኋላ በቆዳው ከረጢት ሰርተው እሱን አሸክመውት ብዙ ስቃይ ተቀብሎ ሰማእትነትን የተጎናጸፈ። 4) ስመዖን(ናትናኤል)፣ መምህረ ሃይማኖት፣ ከጌታ ወንድም ያዕቆብ ቀጥሎ 2ኛ የኢየሩሳሌም ሊቀጳጳስ፣ በመጋዝ የተከፈለ 5) ማቴዎስ፣ አገልግሎቱ በሁሉም ጫፍ፣ የተሰየፈ ሰማእት 6) ፊሊጶስ፣......ቁልቁል ተሰቅሎ ሰማእትነትን የተቀናጀ
Feb 05, 2022