ለAU ስብሰባ የሚዘጉ እና ተለዋጭ መንገዶች ! ጥር 28 እና 29 ቀን 2014 ዓ/ም 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል:: ቀደም ብሎ ጥር 25 እና 26 ቀን 2014 ዓ/ም 40ኛው የህብረቱ አባል ሀገራት የሚኒስትሮች ሥራ አስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይልም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡ በዚህም፦ • ከአዋሬ በጥይት ቤት ወደ ፓርላማ • እንዲሁም ከቡልጋሪያ ወደ አፍሪካ ህብረት የሚወስዱ መንገዶች በሁለቱም አቅጣጫ የስብሰባው ተካፋዮች ጠዋት ለስብሰባ ፣ ለምሳና ከሰዓት በኋላ ከስብሰባ ሲወጡ እነዚህ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ እንግዶቹ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በአጀብ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ለእንግዶች ቅድሚያ በመስጠት ፤ ለአጀብ ስራ መንገድ ሲዘጋ ለተሽከርካሪ ክፍት እስከሚሆን ድረስ አሽከርካሪዎች ትዕግስት ተላብሰው በመጠበቅ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያርጉ ጥሪ ቀርቧል። ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፡- • ከፓርላማ መብራት-በውጭ ጉዳይ ሚ/ር - መስቀል አደባባይ ፍላሚንጎ - ኦምሎፒያ - ወሎ ሰፈር - ጃፓን ኤምባሲ -ፍሬንድ ሺፕ -ቦሌ ቀለበት መንገድ -ኤርፖርት • ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር -በብሄራዊ ቤተ - መንግስት -በፍልውሃ - በብሄራዊ ቲያትር- ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ ፡- • ከፓርላማ መብራት -ብሔራዊ ቤተ-መንግስት - ወዳጅነት ፓርክ - ንግድ ማተሚያ ቤት - ሞናርክ ሆቴል-ቴዎድሮስ አደባባይ-ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል- ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን- ብሔራዊ ቴአትር -ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት • ከፓርላማ መብራት-በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን-ፍልውሃና አምባሳደር ቲያአትር ዙሪያውን • ከንግድ ም/ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ-አፍሪካ ህብረት ዋናው በር-ሳርቤት ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከዓርብ ጥር 27 ቀን / 2014 ዓ/ም ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስከ ሚመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው። • ከጦር ሃይሎች - ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ፦ • በኮካ-ኮላ ድልድይ - በአብነት ተ/ኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር- ጎማ ቁጠባ • ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ፡-ሳር ቤት-ካርል አደባባይ - በልደታ አድርገው ወደ መርካቶ እና ጎማ ቁጠባ • የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች፦ • በአትላስ - ዘሪሁን ህንፃ- ሲግናል • ቀለበት መንገድ - ቦሌ ሚካኤል-ሃኪም ማሞ - ወደ ጎተራ • ቀለበት መንገድ - መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ - እንግሊዝ ኤምባሲ • ቀለበት መንገድ -መገናኛ - አድዋ ጎዳና - አዋሬ - ቤልኤር • በፍላሚንጎ ደንበል ጀርባ መስቀል ፍላወር መጠቀም ይቻላል።
Feb 05, 2022