#ያዕቆብ_ከቤርሳቤህ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወደካራን ሲሄድ የለውም ነበረ አማካሪ ዘመድ ፀሀይ ጠልቃ ነበር ከዛ እንደደረሰ ከእራሱ በታች ድንጋይ ተንተራሰ #አዝ ህልምንም አለመ ታላቁን እራእይ መሠላል ተተክሎ ከምድር እስከ ሠማይ ሲወጡ ሲወርዱ መላእክት በሷላይ እግዚአብሔርም ቆሞ ከላይ ከጫፋላይ #አዝ ያባቶችህ አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ይህን ምድር ለእርስትህ እሰጥሀለውኝ ዘርህ እንደ አሸዋ በምድር ይዘራል በአራቱ ማእዘን ህዝብህም ይሆናል #አዝ አበው በምሳሌ እንደ ተናገሩት ከምድር እስከ ሰማይ አምላክ የዘረጋ በላይ ተቀምጦ በግልፅ የታየባት የያእቆብ መሰላል እመቤታትን ናት #አዝ ሰማይና ምድር የሚታረቁባት ወልድ እጓለመሕያው የተወለደበት መላእክት ከሰማይ ባንድ የዘመሩላት ታላቆ መሰላል እመቤታትን ናት 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️