የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ፡፡አሁን ቤታችን ውስጥ 10 ነን፡፡ቤት ውስጥ ለሚያስፈልገው እያንዳንዱ ወጪ አባቴ ነው የሚያወጣው፡፡እኛ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረን ብሎ በጣም እየለፋ ነው፡፡እናም ተሳክቶለታል፡፡ያው ሰው ሲሳካለት እንቅፋት አይጠፋም፡፡ከዚህ ከዚያም ዘመድ ቤታችን እየመጣ አይወጣም፡፡ጥሮ ግሮ ከመስራት ይልቅ የአባቴን እጅ ይጠብቃሉ፡፡ የአባቴ ገንዘብ የማያልቅ ስለሚመስላቸው ከእሱ ከመጠበቅ በቀር ሌላ አማራጭ የሌለ ነው የሚመስላቸው፡፡በህይወታችን አንድም ቀን አስቤዛ ጠፍቶ አያውቅም፡፡ እንደውም እያማረጥን ነው የምንበላው።ቤታችንን መኪኖቻችንን ብታዩ ሞልቶ የተረፈን ነው የምንመስለው፡፡ነገር ግን በእናቴ ፀሎትና በአባቴ ብርታት የመጣ ነው፡፡የአባቴን እጅ የሚጠብቁ እጆች እያስፈሩኝ ነው፡፡ባይነግረኝም በቅርቡ ገንዘብ አንሶት ከባንክ ተበድሯል፡፡ አባቴ ስለገንዘብ እንዳስብ በፍፁም አይፈልግም፡፡ግን እኔ አለማሰብ አልቻልኩም፡፡ያው መጥፎ ዘመን ስለሆነ እናቴ ወጥታ እንድትሰራ አይፈልግም፡፡ እሷ ደግሞ ይከብደዋል ብላ ስለምታስብ መስራት ትፈልጋለች፡፡ ብቻ እኔ ገንዘብ ጣጣ እንዳያመጣብን እፈራለሁ፡፡ አባቴን ልረዳው ስላልቻልኩ የማይጠቅም ሰው አይነት ስሜት እየተሰማኝ ነው፡፡እናም የኔ ጥያቄ እኔ ከት/ት ሰዓት ውጪ ቤት ሆኜ መስራት የምችለው ስራ ካለ ወይ ደግሞ ት/ት ላይ ጥሩ ስለሆንኩ ማድረግ የምችለው ነገር ካለ እንድትጠቁሙኝ ነበር፡፡ አመሠግናለሁ፡፡🙏
Feb 01, 2022እንዳንተ አይነት አሳቢ ልጅ ስላላቸው ሊኮሩ ይገባል🤗........አንተ ማድረግ ያለብህ ያሳሰበህን ሸክም ሁሉ ለእግዚአብሔር ጣለው እሱ ይወጣዋል እና ፀልይ......እሱ ሚያስደስተው አንተ መርዳትህ ሳይሆን አንተ በርትተህ መማርህ ነው......ብድሩን እንደሚከፍል እመንበት አትጠራጠር ይሄ እሱን ያበረታታዋል
Feb 02, 2022