#አምላኬ_ታሪኬን_ለውጠው አምላኬ /ታሪኬን ለውጠው/(፪) ጌታዬ /ታሪኬን ለውጠው/(፪) ሰው አርገኝና ሰው ይግረመው(፪) እስከመቼ በበደል እስከመቼ በኃጢአት አስመሣይ ማንነቴ ነፍሤን እያሥጨነቃት መሸከም ስላቃተኝ የበዛው እዳዬን በፅድቅ ልመላለሥ ለውጠው መዓዛዬን #አዝ = = = = = ቃልህን ልኑረው በእድሜ በዘመኔ ታሥባለህና ከኔ በላይ ለኔ የፍቅር ሠው ልሁን ደግሞም የይቅርታ የሚሣንህ የለም ታስችላለህ ጌታ #አዝ = = = = = በፍምህ ይዳሠሥ የኃጢአት ለምፄ በቃልህ መዶሻ ይስተካከል ቅርፄ ቀራጩን ለክብርህ ታንበረክካለህ ሠው ታደርገውና ሠው ታስገርማለህ #አዝ = = = = = ፍሬ እንዳላፈራ በሾህ መታነቄ አጥብቀህ ሥጠራኝ አብዝቼ መራቄ በቃ በለኝ ጌታ ልቤን አነሣሣው በመንፈሥህ ቃኘኝ ኃጢአቴን ድል ልንሣው #አዝ = = = = = የኋላዬን ትቼ ወደፊት ልዘርጋ ዋጋ እዳላሣጣው የደምህን ዋጋ እዳሸንፍ እርዳኝ ሥምህን ታጥቄ ዳግም ባሪያ እዳልሆን ልጅነትን ንቄ(፪) ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ