#NewsAlert የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ለሁሉም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና እንደሚሰጥ ተገለፀ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ በተቋማት ተጠያቂነትና የመረጃ ፍሰትን ለመዘርጋት እንዲሁም ውጤታማ እና ቀልጣፋ ሥራ እንዲያከናወኑ ያስችላል በተባለ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ መዋቅር ላይ ያተኮረ ነው። በመንግስትም ሆነ በግል የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ወደሚፈለገው ደረጃ ከፍ ለማድረግ በቀጣይ የትምህርት ዘመን የመውጫ ፈተና ለሁሉም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ሊሰጥ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡ #MoE Can some kne explain what this is about
Feb 01, 2022ከተመረቅክ በኋላ የመውጫ ፈተና ትወስዳለህ። just like ጤናዎች CoC እንደሚወስዱት
Feb 01, 2022