እኔ የኘሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነኝ እና በእኛ ሃይማኖት ዘፈን አይፈቀድም (ስለ ኢየሱስ ያልሆነን ሙዚቃ አንሰማም)፡፡እኔ እስከማውቀው ድረስ በሌሎች ሃይማኖቶችም አይፈቀድም። ግን በብዛት ሰዎች ልክ እንዳልሆነ እያወቁ ምንም ሳይመስላቸው ያዳምጣሉ። በ "YouTube" እንኳን ብናይ ከፍተኛ የእይታ መጠን ያላቸው ዘፈኖች ናቸው፡፡ያሳፍራል፡፡ ማለት ፈጣሪን የሚያከብሩ ስንት የሚያፅናኑ ፣ የሚባርኩ ፣የሚያስደስቱ ፣ ቅድስና የተሞላባቸው መዝሙሮች እያሉ የዘፈን ተመልካቾች መብዛታቸው ምንም ስሜት አይሰጥም፡፡በአንዴ እግዚአብሔርንም ሰይጣንንም ማምለክ አይከብድም?ሀጥያታችን ይቅር ይባላል ብለን ደጋግመን መስራት ልክ አይመስለኝም፡፡ ሌላው ጥያቄዬ ደግሞ የእኛ እምነት ያልሆነን መዝሙር ከማዳመጥ እና ዘፈን ከማዳመጥ የቱ ነው የሚሻለው?
Jan 31, 2022ዘፈን ይለያል ለሀገር ከሆነ ዉበት እሚያደንቅ ከሆነ ለሀጥያት እማይገፋፋ ከሆነ ችግር የለዉም ለዚህም " ብርንና ወርቅን የከበረውንም የነገሥታትና የአውራጆችን መዝገብ ሰበሰብሁ፤ አዝማሪዎችንና አርሆዎችን የሰዎች ልጆችንም ተድላ እጅግ የበዙ ሴቶችንም አከማቸሁ። " (መጽሐፈ መክብብ 2:8) ሰለሞን አዝማሪ ነበረዉ አዝማሪ ምን ይሰራለታል? ሲቀጥል መኃልይ መኃልይ መዝሙር ነዉ ሰም ወርቅም ቢኖረዉም ሰሙም ወርቁም ነዉር የለበትም ዳዊት ስለ ሀገሩ ዘምሩዋል ስለ እየሩሳሌም ደሞ እንዲ ይላል ብለን አናግበስብስ አደራ ... የናንተ መዝሙር አምልኮ ነዉ የናንተን ኢየሱስ ሌላዉ ክርስቲያን አያቀዉም ማለት ልዩነት አለ በ እናንተ እና በሌላዉ ኢየሱስ መካከል ሴጣን አጣሞት ቃሉን የተለየ ኢየሱስ እንደሰራላችሁ ነዉ ሌላዉ ሚያምነዉ ከሀጥያት የከፋዉ ደሞ አምልኮ ነዉ የናንተን ከመዘመር መዝፈኑ ይሻላል .....
Jan 31, 2022