ሰላም ለሁላቹም ይሁን እና እኔ የ 11ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ እስከ ዘጠነኛ ክፍል ድረስ አሪፍ ሳይሆን ጀግና የምባል ሴት ተማሪ ነበርኩ ከዛ በሁአላ ግን ለማንበብ ያለኝ ስሜት ይቀንስ ጀመር ከምላቹ በላይ እራሴን አዘቅጥ ውስጥ አገኘውት ከነበርኩበት የከፍታ ማማ ወርጄ እንኳን ላመጣው ይቅርና ሰው ሲያመጣው የማፍርበትን ውጤት አመጣው ግን እንደዛም ሆኖ እየተማርኩ ነው የሆነ ጊዜ እራሴን ላጠፋ ሞክሬ ነበር ከሞት ነው የተረፍኩት እንደዛም ሆኖ ግን ምንም የመነሳሳት ስሜት የለኝም የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኔ መጠን ቤተሰብ ከኔ ሚጠብቀው ነገር አለ በተለይ አባቴ ደክሞ ስለሚያስተምረኝ የሱን አይን ማየት ይከብደኛል በሚቀጥለው ሳምንት final ነን ግን እኔ ይሀው ቁጭ ብያለው ምን እጄን እንደሚይዘው አላውቅም እስቲ እባካችሁ ትንሽ ሃሳብ ሼር አርጉኝ እኔ እህታቹ በጭንቀት ላብድ ነው
Jan 30, 2022zi_z ሂወትን አንዴ ልትኖሪያት ስንት ጊዜ አማረሽ ታውቂያለሽ ለመቀየርስ ምን ያክል ጥረት አድርገሻል ያንች የሆነው ሁሉ ያንች ነው የተሰጠሽን ለማግኘት ደግሞ ፈተናውችን ችግሮችን ቻሌንጆችን ማለፋ አለብሽና ምክንያቱም አንችን የሚጠብቅሽ ትልቅ ስጦታ ነው ለምን እራስሽን ለማጥፋት ሞከረሽ esti ንገሪኝ...... አንድ ቀን ባደርን ቁጥር ከ እድሚያችን አንድ ቀን እየቀነስን መሆኑን መረዳት አለብሽ ታዲያ ለምን ተመስገን የተሰጠኝን እንዳውቀዉ በስህተት መንገድ እንዳልጓዝ ማስተዋሉን ስጠኝ በይው የሚሳነው ነገር የለም እህቴ የኛ እምነት ማነስ እንጅ የሚሳነው ነገር የለም 🙌
Jan 31, 2022