Eski arif yemtawukutin yefikr tarik kalachihu agaregn aschekuay new
Jan 25, 2022ሁለት ፍቅረኛሞች ነበሩ፤በጣም ይዋደዳሉ።ከእለታት በአንድ መጥፎ ቀን ግን የመኪና አደጋ ይደርስባቸውና ሆስፒታል ይገባሉ። በአደጋው የሚስትየው ፊት እጅግ ይበላሻል፤እሷም ከሰመመኗ ነቅታ የሆነችውን በተመለከተች ግዜ በጣም ደነገጠች፤አዘነች።ከሁሉም ግን ያሳሰባት ነገር ፍቅረኛዋ የፊቷን መበላሸት ቢመለከት እንደ በፊቱ ይወዳት ይሆን ወይ ሚለው ነበር። ፍቅረኛዋ በአንድ ነርስ ድጋፍ ወደ እሷ መጣ ፤እሷ ግን ገና መምጣቱን ስታይ እጅግ ተሸማቀቀች ፡ጀርባዋን ሰጠችው ፊቶቿንም ለመሸፈን ትሞክር ጀመር፤አላስችል ሲላት አምርራ አለቀሰች።ፍቅረኛዋም ውዴ ለምን ታለቅሻለሽ ብሎ ይጠይቃታል፤እሷም ሳግ እየትናነቃት ከዚ በኃላማ ውድህ ልሆን አልችልም፤የምትወደው መልኬ አሁን አብሮኝ የለም፤ፊቴን ሳትመለከት ሂድ ትለዋለች።ውዴ አታልቅሺ አሁንም በህሊናዬ ቆንጅየዋ ፍቅሬ ናት ምትታየኝ፤በአይኖቼ ግን ጨለማን ብቻ እምመለከተው፤በአደጋው የአይኖቼን ብርኃን አጥቻለው አላት።በጣም ደነገጠች በፍጥነት ፊቷን ወደ እሱ አዞረች፤ ስትመለከተው አልቻለችም እጅግ አለቀሰች። ከሆስፒታል ወጡ ፤ይፈርሳል ተብሎ የታሰበው ፍቅር በእሱ ልብ ሰባሪ ንግግሮች ታደሰ፤እሷ መልከ ጥፉ ብትሆንም እሱም ማየት እንደማይችል፤አይኖቹን እንዳጣ ነግሯታልና። በጋብቻ ተሳሰሩ፤ ከበፊቱ እጅግ አብልጣ ትንከባከበዋለች ፤ እሱም "ከሚታየኝ ጨለማ በላይ ትልቅ ብርሀን ነው ሚታየኝ፤ያንቺ ውበት" እያለ ሁሌም ስለ ቁንጅናዋ እና ውበቷ ይነግራታል ።ረጅም አመታትን ፍቅራቸው ሳይቀንስ አብረው ኖሩ ፤ ታዲያ ግን ሞት አይቀርምና እሷ ታርፋለች። ሚስቱ ከሞተች በኋላ ግን ባል ሁሉንም ነገር መመልከት፤ማየት ጀመር።ቀድሞውንስ የእሱ አይን መች ማየት ተሳነውና፤ ያኔ ከአደጋው በኋላ የፍቅረኛውን ጭንቀት ሲመለከት እና የሷን በእሱ ፊት በመልኳ መሸማቀቅ ሲመለከት የወሰነው ውሳኔ ነው እንጂ።ከዛም በኃላ እሷ ትሸማቀቅበት የነበረውን መልክ እሱ ግን እንደ በፊቱ በፍቅር ይመለከተው ነበር፤ስለ ቁንጅናዋ እና ውበቷ ሲነግራት እሱ እንደሚለው በህሊናው ሳይሆን የእውነት በአይኑ እየተመለከታት ነበር።እሷም ፍቅረኛዋ፥ባሏ አይነ ስውር እንደሆነ እያሰበች ፍቅሯ ሳይቀንስ ትንከባከበው ነበር።
Jan 26, 2022