በቅድሚያ ሰላማችሁ ይብዛ በአለም ዳርቻ ያላችሁ በሙሉ አንድ ጥያቄ ነበረኝ በተለይ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ብትመልሱልኝ ደስ ይለኛል ምን መሰላችሁ መፅሀፍ ቅዱስ የምታምኑበት የእምነታችሁ መመሪያ መፅሀፍ መሆኑ ምንም የሚያጠራጥር ነገር አይደለም ። ታድያ ከኦሪት ዘ ፍጥረት እስከ ራየ ዮሀንስ እየሱስ እኔ አምላክ ነኝ ብሎ የተናገረበትን አንቀፅና ምእራፍ የሚነግረኝ ማንም ሰው አጣሁኝ ሌላው ከዚሁ ሳልወጣ ከልጅ ልጅህ ተወልጀ አድናሀለሁ የሚለውስ የት አለ ??? ያልጠየኩት ድያቆን ያልጠየኩት ቄስ የለም የቀረኝ አቡነ ማቲያስ ብቻ ነው ታድያ ካለ ወይም ተናግሮ ከሆነ እየሱስ ለምን አይመልሱልኝም ??? ባለፈው ቁልቢ ገብርኤል ውስጥ በጣም ትልቅ ቦታ በብዙ ቦታ በዋልድባ በጣና ዘጌ በደብረ ሊባኖስ በብዙ ቦታዎች ከ40 አመታት በላይ ለቤተክርስቲያን ሲያገለግል ነበረ በመፅሀፍ ቤት ላይ ከባድ ጥያቄ ይነሳል በዛ ምክንያት ብዙ ቄሶች ብዙ ድያቆኖች ከእምነቱ ለጥያቄዎቻቸው መልስ እያጡ በብዛት ወደ ሌላ እምነት እየሄዱ ነው ታድያ ለምን ጥያቄዎቻቸው አይመለሱም ??? አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏 ስድብ አልፈልግም ስድብ የሽንፈትና የእውቀት ማጣት ድርቀት መሆኑ ለማንም ግልፅ ነው
Jan 24, 2022ራእይ 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁷ እነሆ፤ በደመና ይመጣል፤ የወጉት እንኳ ሳይቀሩ፣ ዐይን ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከእርሱ የተነሣ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎ! ይህ ሁሉ ይሆናል፤ አሜን። ⁸ “ያለውና የነበረው፣ የሚመጣውም፣ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ፣ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ” ይላል። ዮሐንስ 1 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ² እርሱም በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ። ³ ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ ከተፈጠረው ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም። ዮሐንስ 8 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵⁸ ኢየሱስም፣ “እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ፣ እኔ ነኝ” አላቸው። ⁵⁹ በዚህን ጊዜ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወረባቸው፤ ከቤተ መቅደስም ወጥቶ ሄደ። ዮሐንስ 10 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁵ ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሳላቸው፤ “እኔ ነግሬአችሁ ነበር፤ እናንተ ግን አታምኑም፤ በአባቴ ስም የማደርጋቸው ታምራትም ስለ እኔ ይናገራሉ፤ ²⁶ እናንተ ግን በጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም፤ ²⁷ በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔ ዐውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል፤ ²⁸ እኔ የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፤ ከቶ አይጠፉም፤ ከእጄም ሊነጥቃቸው የሚችል ማንም የለም። ²⁹ እነርሱን የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፤ ከአባቴም እጅ ማንም ሊነጥቃቸው አይችልም። ³⁰ እኔና አብ አንድ ነን።” ³¹ አይሁድ ሊወግሩት እንደ ገና ድንጋይ አነሡ፤ ³² ኢየሱስ ግን፣ “ከአብ የሆኑ ብዙ ታላላቅ ታምራትን አሳየኋችሁ፤ ታዲያ ከእነዚህ ስለ የትኛው ትወግሩኛላችሁ?” አላቸው። ³³ አይሁድም፣ “የምንወግርህ፣ ተራ ሰው ሆነህ ሳለህ፣ ራስህን አምላክ በማድረግ፣ የስድብ ቃል ስለተናገርህ ነው እንጂ ከእነዚህ ስለ የትኛውም አይደለም” ብለው መለሱለት። ዮሐንስ 13 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹² እግራቸውን አጥቦ ካበቃ በኋላም፣ ልብሱን ለብሶ ተመልሶ በቦታው ተቀመጠ፤ እንዲህም አላቸው፤ “ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን? ¹³ እናንተ፣ ‘መምህርና፣ ጌታ’ ትሉኛላችሁ፤ ትክክል ነው፤ እንደምትሉኝ እንዲሁ ነኝና። ¹⁴ እንግዲህ እኔ ጌታችሁና መምህራችሁ ሆኜ ሳለሁ እግራችሁን ካጠብሁ፣ እናንተም እንደዚሁ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባችኋል። ¹⁵ እኔ እንዳደረግሁላችሁ እናንተም እንደዚሁ እንድታደርጉ ምሳሌ ትቼላችኋለሁ። Lelam bezuuu metkes yechalal gin atamnum. Eysus Mejemeriyam Fetsum Amlak new..Sew Yehonew gen sel ante, anchi ena ene sil le Bedelachen ena hatiyatachen be sew amsale meta, tesekel, be sosetegnaw kene kemote tensa.
Jan 24, 2022