ምን መሰላቹ የድቁንና ትምህርት እማራለው ግን ብዙ ሀሳብ አይምሮዊ ውስጥ ይመላለሳል በቃ "ወጣት አይደለክ ያውም የሀይስኩል ተማሪ በቃ ፋሽን ተከተል ለምን ጂም ጀምረክ ግብዳ አትሆንም በቃ ፊልም ካላየው ምሞት ነው ሚመስለኝ በቃ ለምን የሙዚቃ ላይሪክስ አሸመድድም በቃ ፈታ በል አዳዲስ ሴቶችን ተዋወቅ ፋቅረኛ ያዝ ይለኛል" አልፎም ምንም ዲያቆን አልመስልም ስፈልግ ስለ ሴት አወራለው ግራ እንደሚገባቹ አውቃለው እስኪ ምከሩኝ እንዴት እዚ ምድር ላይ በመንፈሳዊ ህይወት መኖር ይቻላል? ከቻላቹ በደንብ ብታስረዱኝ
Jan 22, 2022ድቁና ከመቀበልህ በፊት በጣም ፈተና ሚሆነው ይሄ ነው chik መያዝ sex ማድረግ ብቻ አለማዊው ነገር ከ ሌላው ቀን በተጨማሪ ያምርሀል ከሚባለው በላይ ድቁና ተቀብለህ ደሞ ትእቢት በጣም ይፈታተነሀል አውቃለው ባይነት ታበዛለህ ሌላውን ምእመን እንደተራ ነገር ትቆጥራለህ ቤተ መቅደስን ተትዳፈራለህ ለምን? ምክንያቱም ይሄ ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ስልጣን ስለሆነ ሴይጣን ደሞ ይሄን አይፈልግም ስለዚ ድቁና ሳትቀበል በ ስጋዊ ፍላጎት ድቁና ስትቀበል ደሞ ትእቢትን ውስጥህ እንዲያድር በማድረግ በሚገርመው ሁኔታ ድቁና ስትቀበል ያልካቸው ሁላ ነገሮች አታስታውሳቸውም ምክንያቱም በ አንተ ላይ ሚያድረው ቅዱስ መንፈስ ሀይለኛ ስለሚሆን ነገር ግን ፀሎት ከሌለበት ትልቅ ትዕቢት ያመጣል እና ወንድሜ ከቻልክ አትግባ እሳት ነውና አፈርሳለው ሚል ፍርሀት ካለብህ ግን ደሞ ፈጣሪን ማገልገል ከፈለክ ደሞ በ ፀሎት ትጋ በመጨረሻም ግን ሀይማኖት ከዘመኑ ጋር ይሄዳል ነገር ግን ከ ሀይማኖት ባላፈነነጠ መልኩ ፋሽን ልትከተል ትችላለህ ግን ልብሱ ምን አይነት ነው?ስለ ሴት ልታወራ ወይም ጉአደኛ ልትይዝ ትችላለህ ነገር ግን ምይዘው ፍቅረኛ ዝም ብሎ ለ ሙድ ነው ወይስ በ ተክሊል ለማግባት?ዘፈን ሸምድደህ ከመዋል እና አንድ ውዳሴ ማሪያም ዜማ,ቅዳሴ መሸምደዱ ይሻላል?ማየው ፊልም እራሴን ለማዝናናት ነው ወይስ sex ለማየት?በመጨረሻም ድቁናውን የፈለኩት ፈጣሪን በ ፍርሀት ለማገልገል ነው ወይስ ለ ታይታ ነው? እነዚን ጥያቄዋች ከራስህ ጋር ተወያይባቸው ከዛ የራስህን ውሳኔ ትወስናለህ እመቤቴ ትርዳህ 🙏
Jan 23, 2022