የእኔ ጥያቄ ለውድ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ነው፡፡ እኔ ከተፈጠርኩ ጀምሮ ጴንጤ ነኝ ግን ኦርቶዶክሶችን በጣም ነው ምወዳቸው፡፡ በጣም የምወዳቸው እነሱን ለመጥላት ምክንያት አጥቼ ሳይሆን ኢየሱስ ፍቅርን ስላስተማረኝ ነው፡፡ ግን ሁሉንም ማለት ቢከብደኝም አብዛኛው ኦርቶዶክስ ጴንጤን አይወድም፡፡ አንዳንዶቹማ ከመጠን ያለፈ ጥላቻ ነው ያላቸው፡፡ለምን? ማለቴ እኛ ክርስቲያኖች ነን፡፡ የምንሰብከው ወንጌል ነው፡፡ ወንጌል ደግሞ እናንተም የምታውቁት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የማይሻር አውነት ነው፡፡ እንደውም እኛን በተለየ ሁኔታ መውደድ ነበረባችሁ፡፡ እኛን ለመጥላት ያደረሳችሁን ምክኒያት ብትነግሩኝ፡፡ ሌላው ደግሞ እኛ በኢየሱስ ስም ፣ ኢየሱስ ጌታ ነው እያልን ስንሰብክ ጌታ መሆኑን እያወቃችሁ ትቃወማላችሁ ለምን? በመጨረሻም እኛ ክርስቲያናች ነን እርስ በእርስ መደጋገፍ አለብን፣ ክርስቲያን ላልሆኑ ሁሉ የፍቅር ምሳሌ መሆን አለብን ብዬ አስባለው አመሠግናለሁ፡፡ ተባረኩ!!!
Jan 20, 2022Ene be gele aletelachehum gn egna ende ayenachen yemenayaten maryamn atakebrum ena bezi meknyat enekarenachuhalen
Jan 20, 2022