አብዛኛዎቹ ሴቶች ወንድን ልጅ ቢወዱት እንኳን ልጁን ለማመን ይከብዳቸዋል። normally ለ s*x ቀርቦኝ ቢሆንስ የሚል ስጋት አላቸው። ግን normally ወንድ ልጅ ሴትን ለጥቅም እንዲቀርባት ያደረገው ነገር ምን ይመስላችኋል? እንደ እኔ የ environment ጫና ይመስለኛል። እናንተስ ምን ትላላችሁ?? Tnx for the anwsers.
Jan 16, 2022ተፈጥሮ ነው ምን ይደረጋል። ራሱንና ስሜቱን መቆጣጠር የማይችል ከኾነ ሴትን የሚፈልገው ለጥቅም ብቻ ነው። ደግሞም በአሁኑ ዘመን ስሜትህ እንዲያይል መቆጣጠር እንዳትችል የሚያደርጉህ ብዙ ተጽኖዎች አሉ። ዓለሙ ሴትን እንደሰውነነቷ ሳይኾን ለራስህ እርካታ እንደምትጠቀምባት እቃ አድርጎ ያሳይሃል። environment ያልከው እንደሰዉ ይለያያል። እናትና አባቱ ተከባብረው ተዋደው እየኖሩ የሚያይ ወንድ ወደመጥፎ አስተሳሰብ የማምራት እድሉ ዝቅተኛ ይመስለኛል።
Jan 17, 2022