ሰላም ውድ የ ኢትዮጵያ ልጆች።🙏 ዛሬ ትንሽ ጥያቄ የጫረብኝን ነገር ልጠይቃቹ ነው። እኛ ሰዎች ስንሞት ነፍሳችን እንደ ስራችን ልክ ተዳኝታ ወይ ሲዖል ወይ ደሞ ገነት ትላካለች። what about እንስሳት? I mean እነሱ ሲሞቱ ነፍሳቸው ወዴት ነው ምትሄደው? ወይስ የእነሱም ነፍስ እንደ ሰው ይዳኛል? ስለ ምላሻቹ አመሰግናለው🙏🙏
Jan 15, 2022በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ መሰረት የእንስሳት ነፍስ ደማዊት ነፍስ (እንደ እኛ ያልሆነ ማለትም ደመነፍሳዊ ህይወት ስለሆነች) በፍርድ ጊዜ ምንም አይነት ፍርድ የለባትም። ስለዚህ በዚያን ጊዜ የሰው ልጆች ሁሉ ለፍርድ ሲነሱ እንስሳት ግን እንደሞቱ (በስብሰው)ይቀራሉ።
Jan 15, 2022