ፍቅረኛየ ከሌላ ወንድ ጋ ለረጅም ሸአት ስልክ ታወራለች አና ተነጋግረን ልንፈታው አልቻልንም አየቀናሁ ይሆን ብየ ላልፈው ሞከርኩ ግን አልቆመም ምን ላድርግ?
Jan 14, 2022በግሌ እኔም ደስ አይለኝም እሷን ላምናት ብችልም ደዋዩን አላምነውም። ፍቅር አይቀናም ብዬ ሲደጋገም ላልፈውም ሆነ ልተወው አልፈልግም።ፍቅር የማይቀናዉ ከዚህ አንጻር አይደለም።እኔ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝ ይላል።ለሱ መስገድ ሲገባን ለጣኦት ብንሰግድ ይቀናል።ከኔ ጋር ብቻ እንደዛ ማውራት ሲኖርባት ከሌላ ጋር ብታደርገው እቀናለው። በመሆኑም የማደርገው በቅድሚያ እንድትተው በመንገር ከሱ ጋር ያላቸውን ቀረቤታ እንዲቀንሱ አስጠነቅቃለው። ይህን የማደርገው እሷን የመጠበቅ ግዴታም ስላለብኝ ነው። አይሆንም ብላ ከገፋችብት ልትሰማኝ እና ልትቀበለኝ ባልወደደች መጠን እርቃታለው። ጠልቻት ሳይሆን ወዳልተገባ ቅናት እንዳላመራ ስል ነው።
Jan 15, 2022