Sewoch Hirut Abatua Manew ambassador cinema lay sint seat new mitayew? Ketechalem ye mastawekiyaw picture binor tiru new.
Jan 14, 2022ኂሩት አባቷ ማነው? ትኬት ሽያጭ 1. በሸራተን አዲስ 2. በፍሬንድሺፕ ፓርክ 3. በመስቀል አደባባይ ዲያሰፖራ ሴንተር 4. በሲኒማ አምፒር 5. በሲኒማ ኢትዮጵያ 6. በሲኒማ አምባሳደር መሆኑን በትህትና እንገልጻለን ያለን ውስን ቦታ በመሆኑ ፈጥነው በመግዛት በታሪክ የመጀመርያውን ፊልም ለማየት ዕድለኛ ይሁኑ፡፡ *** የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሂሩት አባቷ ማነው የተሰኘውን ፊልም በ1956ዓ.ም ለቀረበለት ጥያቄ ፋይናንስ በማድረግ ፊልሙ እንዲሰራ ትልቁን ሚና ተጫውቷል፡፡ በመቀጠልም ከሃምሳ ዓመታት በኋላ በ 2006 ዓ.ም. ከመጋቢት ወር መጨረሻ እስከ ሰኔ መጀመሪያ፣ በአዲስ አበባ በኢዮሀ ሲኒማ አነሳሽነት እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተባባሪነት ተዘጋጅቶ በነበረው “የኢትዮጰያ ፊልሞች ፶ኛ ዓመት ኢዮቤልዩ” ክብረ በዓል መክፈቻ ላይ የ“ኂሩት አባቷ ማነው?” ሥነ ራዕይ ለየት ባለመልኩ መክፈቻው ሲታወስ፣ ከሃምሳ ዓመት በፊት ሥራው ሲከናወን በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከ40 ዓመት በላይ ፊልሙ ሳይበላሽ በጥንቃቄ በባንኩ እጅ ቆይቶ በሃምሳኛው ዓመት ለታሪክ ማስታወሻነት ባንኩ የጥበብ ሥራው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይደረስ ዘንድ ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር በሥጦታ በታላቅ ኩራት ለግሷል፡፡ ዛሬም ይህ ፊልም ጥር5/2014ዓ.ም አምሮበት ከፍ ባለ ደረጃ እንዲመረቅ ከአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት፤ ከአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ለዚህ አብቅቶታል፡፡ ይህ ልማት ድርጅት ለአርቱ ማህበረሰብ ትልቁን ድርሻ ተወጥቷል፡፡ በመሆኑም ፊልሙ በሚታይባቸው ቦታዎች ጥር 5/2014ዓ.ም በሸራተን አዲስ ጥር7/2014ዓ.ም በብሔራዊ ቲያትር፤ በአምባሳደር ቲያትር፤ በአምፒር ሲኒማ እና በኢትዮጵያ ሲኒማ በድምቀት ከ7፡30 ጀምሮ ስለሚታይ ሁላችሁም ለማየት ትሽቀዳደሙ ዘንድ በታላቅ አክብሮት ከአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ፤ የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ይጋብዛል፡፡
Jan 14, 2022