ሁሌ የሚያስጨንቀኝ ነገር አለ!! አስቀያሚነቴ ስነልቦናየ እጅጉን ተጎድቷል ሰዎች ብዙ አይቀርቡኝም ያልሆነ ዝቅተኛ ግምት ይሰጡኛል!! ከስቃይ የሚገላግለኝ ምክር ካላችሁ
Jan 08, 2022ወንድ ከሆንክ ውበት ያን ያህል ሊያሳስብህ አይገባም!!!..... ሴት ከሆንሽ ደሞ ውጫዊ ውበትሽ በሰዎች ላይም ሆነ በራስሽ ላይ የሚፈጥረው ተፅእኖ ከፍተኛ የሚባል ነው ለሞራልሽ አስቤ ላሞኝሽ አልፈልግም ግን የምመክርሽ ነገር ቢኖር ሰዎች ለራስሽ የምሰጪውን ቦታ አይተው ነው የሚያከብሩሽ የሚንቁሽ እና ሌላም ሌላም ስላንቺ የሚስማቸው ያው ባለቤቱ ያቀለለውን ባለዳ አይቀበለውም አደል ተረቱስ😉.... ያማለት እንሱ የሚሰማቸው ነገር በሙሉ የራስሽ እጅ አለበት!!....እና በአጭሩ ለራስሽ ያለሽን አመለካከት ቀይሪ ከሰዎች ጋር ያለሽንም ተግባቦት በመጠኑ አሳድጊ የሚንቁሽን ሰዎች ገደል እንዲገቡ ምከሪያቸው👉...ደሞ ያን ያህል አስቀያሚ የምትባይ አደለሽም እርግጠኛ ነኝ! ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ቁንጅና አለው ውስጣዊ ውበት ምናምን እያልኩ አላጃጅልሽም ነገር ግን ምንም እንኳን ቆንጆ ባይሆኑም ባህሪያቸው አሪፍ እና ተጫዋች የሆኑ ሰዎች በቀላሉ ሰዎችን እንደሚስቡ እንዲሁ ከህይወት ልምድሽ መረዳት የሚከብድሽ አይመስለኝም 🤷♂ ...ስለዚ አሁን ምን እያልኩሽ እንደሆነ እየገባሽ ይመስለኛል ስለማይቀየረው ውጫዊ ውበትሽ ማሰቡን ትተሽ በትንሽ ጥረት እና ልምምድ ስለምቀይሪው ወስጣዊ ውበትሽ(ውስጣዊ ውበት ከምንለው ባህሪ እንበለው!) አስቢ!!!😊 ደሞ ሰዎች ምንም ቢሉሽ በራስሽ ላይ ያለሽን አመለካከት እንዲሸረሽር እንዳታረጊ አደራ !✋ሰዎ አምሮብሽላ እስካላለሽ ድረስ እንዳላማረብሽ ካሰብሽ በቃ ተበልተሻል😁....ደስታሽን በሰዎች እጅ ላይ በፍፁም እንዳታረጊ!!!!! መልካም ዘመን አስጠሊዋ✋😐
Jan 08, 2022