ሰላም ሰዎች🤚 ምን መሰላችሁ በጣም ምወደው ጓደኛ አለኝ ከጓደኛም አልፎ እንደ ወንድም ነው የማየው እና በጣም ክሎዝ ነን በጣም ሲበዛ እንቀራረባለን ሁለታችንም ፍቅረኛ አለን እኔ እሱን እንደምቀርበው ራሱ ፍቅረኛዬን አልቀርበውም እሱ በጣም ሚወዳት ለሱዋ ሲል ምንም ሚያደርግላት ልጅ አለች ግን ሰሞኑን ፀባዩ እየተቀየረብኝ ማለት ከበፊቱ ይልቅ በጣም እየቀረበኝ እና ንግግሩም ወደ ፍቅር አይነት ወሬ እየሄደብኝ ነው እና ጥያቄው ይሄ ልጅ ምን አስቦ ሊሆን ይችላል ከኔ ጋር ሌላ ነገር አስቦ ከሆነ ያቺ የሚያፈቅራት ልጅስ ብቻ ግራ ገብቶኛል ምን ትላላችሁ
Jan 07, 2022እስኪ አንቺ ማንን ነው የምትፈልጊው 😊 ማለቴ ከኔ ጋር ሌላ ነገር አስቦ ከሆነ ያቺ የሚያፈቅራት ልጅስ ሰትይ የገባኝ እሷ እንዳትጎዳ ብለሽ እንጂ አንቺ ጋር አንድ የሆነ የደበቅሽው ስሜት እንዳለ አይነት ነው። በአጭሩ እስኪ ጥያቄሽን ላስተካክልልሽ እና ይኽን መልሽልን ራስሽ #ከበፊቱ ይልቅ በጣም እየቀረበኝ እና ንግግሩም ወደ ፍቅር አይነት ወሬ እየሄደብኝ ነው እና ጥያቄው ይሄ ልጅ ምን አስቦ ሊሆን ይችላል ከኔ ጋር ሌላ ነገር አስቦ ከሆን እኔ #አልፈልግም እና ምን ላድርግ ወይም #እፈልጋለው እና ፍቅረኛዬን ምን ብዬ ልተወው እና ከእሱ ጋር ልሁን. . . . በይ እስኪ አንዱን
Jan 07, 2022