#Update የአማራ ክልል መንግሥት አስተዳደር ም/ቤት ከአሁን ቀደም የሰዓት እላፊ ገደብ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡30 መንቀሳቀስ እንደማይቻል ውሳኔ በማሳለፍ በክልሉ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ እንደገለጹት ከአሁን ቀደም ተጥሎ የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ ሙሉ ኃላፊነት ለከተማ አስተዳደሮች በመስጠት የፀጥታ ሁኔታውን እየገመገሙ በራሳቸው ሰዓት እላፊ ገደቡን የማንሳትም ሆነ የማስቀጠል ሙሉ ኃላፊነት ከተጠያቂነት ጋር የተሰጣቸው መሆኑን የክልሉ መንግሥት አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ አስተዳደር ምክር ቤቱ አሁን ያለውን ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው የሰዓት እላፊ ገደቡን በተመለከተ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ሲሉ አቶ ግዛቸው መናገራቸውን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል። if you get my answer useful can i get ✅✅✅✅✅ tnx 😉😉😉😉😉
Jan 07, 2022