I've always been curious about the concept of masturbating Some say it's a sin while some dont Eski sin new yemitilut ,where in the bible does it actually say that Maybe it's because of lust litichilu tichilalachu but people can masturbate with out lust Ena for the ones that say it's not a sin What made u start doing it This is for both guys and girls And please dont come at me I was just trying to see people's views on this issue cz not everyone really agrees on one thing
Jul 26, 2020▪️▪️▪️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን። #ጥያቄ_ስለ_ግብረ_አውናን_ብትነግሩን? 'ግብረ አውናን' በእግሊዘኛው 'Masturbation' አንድ ሰው በዝሙት ዝንባሌ ተይዞ ከእንቅልፍ ውጪ ዘርን እያወቁ ወደ ውጪ ማፍሰስ ማለት ነው፡፡ 'ግብረ አውናን' የተባለበት ምክንያት አውናን የተባለው የይሁዳ ልጅ ዘሩን ከሚስቱ ማህጸን ውጪ ያፈሰው ስለ ነበር ነው፡፡ ዝሙትን ወዶ ክቡር ዘርን የትም ማፍሰስና የአውናን ዘሩን ከማህጸን ውጪ ማፍሰስ አንድ ናቸውና፡፡ ዘፍ. 38:9 👉አንድ ገበሬ ለዘር የሚያስቀረው ዘር ራሱ ከሚመገበው እንኳ የተሻለውን ምርጥ ዘር ነው፡፡ ስለሆነው ከዘር በፊት ተጠንቅቆ በሪቅ (በጎተራ) ያስቀምጠዋል፡፡ በዘር ወቅት ደግሞ አውጥቶ በመልካም ማሳ ላይ ይዘራዋል እንጂ ያለቦታው አይበትነውም፡፡ እንዲሁም የሰው ዘር ከእህል ዘር ይከብራልና በመልካም ጎተራ ማለትም በሰውነት ተጠብቆ መቆየት አለበት፡፡ ከጋብቻ በኋላ ባልና ሚስት ሩካቤ ሲፈፅሙ ደግሞ በመልካሟ ማሳ በሚስት ማህፀን መዝራት እንጂ በልዩ ልዩ ምክንያት ሆን ብሎ ዘርን እንደ ጉድፍ ከማህጸን በአፍአ (በውጪ) ማፍሰስ ከባድ ኃጢአት ነው፡፡ አውናን የተባለው ሰው ዘሩን ከማህጸን ውጪ በማፍሰሱ ምክንያት የደረሰበትን መቅሰፍት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይተርከዋል፡፡ "አውናንም ዘሩ ለእርሱ እንዳይሆን አወቀ፡፡ ወደ ወንድሙ ሚስት በገባ ጊዜ ለወንድሙ ዘር እንዳይሰጥ ዘሩን በምድር ያፈሰው ነበር፡፡ ይህው ስራው በእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ ሆነበት እርሱንም ደግሞ ቀሰፈው፡፡" ዘፍ 38:9-10:: ይህ ታሪክ በማንኛውም ምክንያት ዘር አፍሳሽ መሆን ሊያስቀስፍ የሚችል ክፉ ስራ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "እንግዲህ በምድር ያሉትን ብልቶቻችሁን ግደሉ፡፡ እነዚህም ዝሙት ርኩሰት ፍትወት ክፉ ምኞትም ጣዖትን ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው፡፡" ቆላ 3:5 እዚህ ላይ "ብልቶቻችሁን ግደሉ" ሲል ቆርጣችሁ ጣሏቸው ማለቱ ሳይሆን አትቀስቅሱ ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ዘርን ለማፍሰስ ሀፍረተ ስጋን መነካካት ተገቢ አይደለም፡፡ ዳግመኛም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ፡፡" 1ኛ ቆሮ 7:9 ብሏልና በዝሙት ለሚቃጠሉ መፍትሔው ማግባት እንጂ መሰንጋት (ሴጋ መፈጸም) አይደለም፡፡ ሐዋርያውም ይህን እንደ መፍትሔ አልመከረምና፡፡ (ሕይወተ ወራዙት መፅሀፍ፡ ቀሲስ ኅብረት የሺጥላ) ♠ግብረ አውናን መፈፀም ማለት ሰው የመግደል ያህል ሀጥያት ነው ምክንያቱም ያ ዘር ሰው የሚሆን የእግዚአብሔር ስራ ነውና። ይህም ሲባል ሰዎች ተስፋ እንዲቆርጡ ሳይሆን ከዚህ አፀያፊ ተግባር ትውልዱ እንዲላቀቅ እንጂ። ሰው ሊያውም ክርስቲያን መልካም ስራ በመስራት ሊጠመድ ይገባዋል እንጂ እንዲህ በረከሰ ተግባር ውስጥ ሊዘፈቅ አይገባም። ንፁህ ሰዎች ልንሆን ይገባል በዚህ አይነት ተግባር ውስጥ ለተዘፈቁ እህት ወንድሞችም ላይ መፍረድ አይገባም መንገድ ማሳየት እንጂ። በሚቀጥለው ጊዜ ስለ መፍትሄዎቹ እና መላቀቅያ መንገድ እናያለን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር! ወወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ለዓለም ዓለም አሜን። @KaleEgziabeher
Jul 27, 2020