ኢትዮጵያ የሀይማኖት ሀገር ነች ይባላል እናም ክርስትናና /ኦርቶዶክስ,ካቶሊክ,ፕሮቴስታንት.../ እስልምና አማኞች አሏት እናም ሰውን እግዚአብሔር ወይም አሏህ ነው የፈጠረው ብለው ህዝቧቿ ያምናሉ ከዛ ደግሞ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ናት ይላሉ ሉሲ ምናምን ብለው አፅም ያሳያሉ ሰው የመጣው ከዝንጀሮ በዝግመተ ለውጥ ነው ብለን እንድናምን በአለመሰ አቀፍ ደረጃ ያስተምራሉ የት/ት ካሪኩለም ላይም አለ ታዲያ ይሔ ሁለት ነገር አይጋጭም? 😳
Jan 04, 2022መጀመሪያ ማነው ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ናት ወይም ከዝንጀሮ ነው የመጣነው ያለው?? እኔ ነኝ ያልኩት አንተ ወይስ ማን አየህ ኢትዮጵያዊ ስንባል እኛንም ያካትታል። እርግጠኛ ነኝ ሰፈርክ ውስጥ እኔም ሰፈር ፣ ወይም የአብዛኞቻችን ሰፈር ያሉ ሰዎችን ብትጠይቅ ከዝንጀሮ ነው የመጣነው የሚልክን አታገኝም ። ነገር ግን የትምህርት ካሪኩለሙ ላይ ሊኖር ይችላል ምክንያቱም ሳይንስ ያስቀመጠውን ነገር ማስቀመጥ ስለሚኖርበት ያ ማለት ግን እኛ አምነንበታል ማለት አይደለም
Jan 05, 2022