For christians only እንደምታወቀው ለሀይማኖታችን መሠረቱ bible ነው። ግን bible የእግ/ር ቃል ነው ብሎ የነገረን ሰው ነው።(ከሰው ወደ ሰው እየተላለፈ የመጣ ነገር ነው።) ስለዝህ bible የእግ/ር ብሎ ማመን ሰውን ማመን አይሆንም?
Jan 04, 2022በነገራችን ላይ ስለ መጽሀፍ ቅዱስ ስናወራ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር የሚያውቁትን ነገር የጻፉበት መጽሀፍ ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱ ራሱን በሰዎች በኩል የገለጠበት መጽሀፍ ነው ። ስለዚህ በመጽሀፉ አስተማማኝነት እና ኃይለ ቃልነት መጠራጠር የለብንም ። ደግሞም ኢየሱስ ራሱ ሕግም፣ መዝሙር እና ነቢያት ስለ እኔ ይናገራሉ ብሎአል ። ይህ ማለት ራሱ ጌታ መጽሀፍት ስለ እርሱ እንደሆኑ እያስረገጠልን ነው ። ደግሞም ለኃይማኖታችን መሰረቱ ክርስቶስ ነው ። የመጽሀፍ ቅዱስ ዋና ጭብጡም ክርስቶስ ስለሆነ ማለት ነው ።
Jan 04, 2022