ኢሄን ነገር ትክክል ብላችሁ ተቀብላቹሃል? አምላክ ፍቅር ነው ይል አልነበር? እና ለምን ክርስትናን ያልተቀበለ ይገደላል? እሺ በሰው ላይ ቢጨክን እንስሳት ምን አጥፍተው ነው? ዘዳግም 13 6-7 #የእናትህ #ልጅ #ወንድምህ #ወይም #ወንድ #ልጅህ ወይም #ሴት #ልጅህ ወይም በብብትህ ያለች #ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፡— #ና፥ #ሄደን ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀረቡት ከአንተም የራቁት አንተን ከብበውህ ያሉ #አሕዛብ #ከሚያመልኩአቸው #አማልክት፥ አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን #ሌሎች #አማልክት #እናምልክ ብ#ሎ #ቢያስትህ፥ እሺ አትበለው፥ 9 ነገር ግን #ፈጽመህ #ግደለው፤ እርሱን #ለመግደል በፊት የአንተ እጅ፥ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን። 12-13, አምላክህ እግዚአብሔር ልትኖርባት በሚሰጥህ በአንዲቱ ከተማህ፡— ክፋተኞች ሰዎች ከእናንተ ዘንድ ወጥተው፡— ሄደን የማታውቋቸውን ሌሎችን አማልክት እናምልክ፡ ብለው የከተማቸውን ሰዎች አሳቱ፡ ሲሉ ወሬ ብትሰማ፥ 14 ትፈልጋለህ፥ ትመረምራለህም፥ ትጠይቃለህም፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመካከልህ እንደ ተደረገ እርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥ 15, የዚያችን ከተማ ሰዎች #በሰይፍ_ስለት #ፈጽሞ #ትመታቸዋለህ፤ #ከተማይቱን፥ በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ #እንስሳውንም_በሰይፍ ስለት #ታጠፋቸዋለህ።
Dec 31, 2021በመጀመሪያ ደረጃ ይህ የጠቀስከው ክፍል ክርስትና ከመጀመሩ (ክርስቶስ ወደምድር ከመምጣቱ) በፊት የነበረን የአይሁድን እምነት የሚመለከት እንጂ ከክርስትና ጋር በቀጥታ የሚገናኝ አይደለም። ሲቀጥል ደግሞ የክፍሉን አውድ ከተረዳኸው እያወራ ያለው ስለሌላ ህዝብ ሳይሆን እዛው ከእስራኤላውያን መካከል ሌላ አምላክ እናምልክ ስለሚሉ እስራኤላውያን ነው። ስለ እስራኤል ህዝብ ደግሞ ከዘፀዓት መጽሐፍ (ወይም ደግሞ ከዘፍጥረት 12 ከአብርሀም ጥሪ) ጀምሮ ስናይ እግዚአብሔር ለዚህ ህዝብ ምን ያህል እንደጠበቃቸውና እንደሚጠነቀቅላቸው እናያለን። በብቸኛነት ህዝቤ ብሎ ይጠራቸዋል (ዘፀ 3:7) እናም ከግብጽ ባርነት ባወጣቸው ጊዜ ወደ ተስፋይቱ ምድር (የጠቀስከው ክፍል ላይ 'እግዚአብሔር ልትኖርባት የሚሰጥህ ከተማ' የተባለችው) ሲገቡ እንዴት መኖር እንዳለባቸው የሚመሩበት ህግን ሰጣቸው #አስርቱ_ትዕዛዛት (ዘፀ. 20) ከነሱም ውስጥ አንዱ "ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።" የሚል ነው። ስለዚህ ይህ ህዝብ ከሚመራበት ከዚህ ህግ ውጪ ከተገኘ በህዝቡና በህጉ ባለቤት (እግዚአብሔር) ይጠየቃል፣ ይቀጣልም። ሌሎች ህዝቦች ግን እስራኤላውያንን እስካልነኩ ድረስ ከዚህኛው አይነት ህግ ውጪ ናቸው (ያሻቸውን ማምለክ ይችሉ ነበር)
Jan 01, 2022