ሰላም ኢትዮጵያውያን አንዴት ናችሁ? እኔ መጠየቅ የምፈልገው ስለመልካችን እና ማንነታችን ነው፡፡ ማለት እኛ አፍሪካውያን ጥቁሮች ነን ግን ለጥቁር ቀለም ያለን አመለካከት መጥፎ ነው፡፡ ጥቁር እንስሳት የመጥፎ እድል ተምሳሌት ናቸው ይላሉ፣ ጥቁር የሀዘን ምልክት ነው፣ሰይጣን በጥቁር ነው የሚመሰለው (ሰይጣን በነጭ ሲመሰል ሰምቼ አላውቅም) ይህ ሃይማኖታዊ ምክንያት አለው ብትሉ እንኳ እግዚአብሔር እኛን ለምን ጥቁር አድርጎ ፈጠረን? ሌላው ጥያቄዬ ሰዎች በተለይ አፍሪካውያን ለጥቁር ቀለም ያለን አመለካከት ለምን ወረደ? ማለቴ ጥቁር ቀለምን በመልካም መንገድ መመልከት ለምን አቃተን?
Dec 30, 2021ከሰይጣኑ ስጀምር ሰይጣን በተፈጥሮው ሰማያዊ መልአክ እንደመሆኑ በራሱ ጥቁር መልክ የለውም። የሰው ልጅ ሀጢያትን ለመስራት ከብርሀን ይልቅ ጨለማን ይመርጣል የክፉ ስራ ወዳጅ የሆነ ዲያቢሎስም በብርሀን ሳይሆን ጨለማን ተላብሶ ይሳላል ይታሰባል።(ግብርን ሲያጠይቅ ነው)በነጭ ቢመሰል ስለ ቀደመ ክብሩ ብቻ ማንሳት ይሆን ነበር። እግዚአብሔር እኛን ለምን ጥቁር አድርጎ ፈጠረን ላልከው እግዚአብሔር ለምን ነጮቹን ነጭ አድርጎ ፈጠራቸው የሚለውን ምላሽ ብትነግረን ለምን ጥቁር እንዳረገን የምነግርክ ይሆናል። ጥቁር በራሱ የሀዘን ምልክት ያልሆነባቸው ሀገራት አሉ።የሆነ ሆኖ አንድ ሰው ጥልቅ ሀዘን ውስጥ ሲገባ ሰውነቱ የመክሳት ፊቱ የመጥቆር ዝምታን ገንዘቡ ማድረግ ይጀምራል በዚ ግዜ አንድ ሰው በሀዘን ተውጧል ጽልመት ወርሶታል ይባላል በመልክ ላይ የሚታይን ለውጥ ነው በአለባበስ የተገለጸው።ሌላው ጥቁር እንስሳት የመጥፎ እድል ተምሳሌት ናቸው ያልከው ፍጹም ሀሰት ነው። የሀገርክ ጠንቋይ ጥቁር ዶሮ እረድ ስላለ ነጩን ዶሮ የማይመገብ ሆኖ አይደለም በተቃራኒው በብዛት ስለማታገኘው ሊያንከራትትክ እንጂ። ጥቁር አንበሳ ጥቁር (ፓንተር) አማርኛ ስሙ ቢጠፋኝ ነው ባጠቃለይ ጥቁር የተባሉት እንሰሶች ከተለመደው እንስሳዊ ሀይል ባሻገር ውሳጣዊ ኃይል ያላቸው ናቸው። የመጥፎ እድል ተምሳሌት ያደረጋቸው ያጣቸው ሰው ነው። አፍሪካውያን ሁሉም ሀገራት በነጮች ቀኝ ገዢነት ስር የወደቁ በመሆናቸው ለጠቆረ መልካቸው እና ለራሳቸው የሰጡት ግምት ዝቅ እንዲል አድርጓል ኢትዮጵያውያን ከዚ ፍጹም የተለዩ ናቸው ለዚም ነው በተለያዩ ሀገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን በመልካቸው የተነሳ ነጮች አር ዩ አፍሪካን ብለው ሲጠይቋቸው አይ አም ኢትዮጵያን የሚል ምላሽ የሚሰጧቸው😂😂 ባለቅኔ ህዝብ። አንድ እንደማንም አፍሪካዊ ቅኝ አለመገዛቱን ሲነግረው አንድም ደሞ ጥቁርነትን የመጥፎ አልያም የበታችነት አለመሆኑን ሲያሳውቀው ነው።ሚኒሊክ ዛሬም ንጉስ ነው ያለው ዘፋኙ በምክንያት ነው።
Dec 31, 2021