Selam eht wendmoch yihe tiyake le Orthodox tewahdo wendm ehtoche yihunlgn Ena and sew ግብረ አውና(ግለ ወሲብ)fetsimo nsiha bigeba ena rasun tebko binor eskemiyageba betekilil magbat yichlal wey dngl libal yichlal?
Dec 27, 2021ማስተርቤሽን ቪድዮ ሴክስ ፎን ከፈጸሙ በኋላ "በአካል ተቃራኒ ጾታ ጋር ግንኙነት አላደረኩም ተክሊል መፈጸም ይፈቀድልኛል?" የሚል ጥያቄ በአእምሯቸው የሚፈጠረው ፍቅር እግዚአብሔር ሲጎድልብንና ራስ ወዳድ ስንሆን ነው። ምክንያቱም ማስተርቤሽን ቪድዮ ሴክስ ፎን ሴክስ የመሰለ ብዙ ኅቡረ ዝሙት እየፈጸምን ያሳስበን በደልነቱ ሳይሆን ተክሊል መፈጸም አለመፈጸም መሆኑ ነው። እንዲህ አይነት አስተሳሰብ "የቤተ ፈት" አስተሳሰብ ይባላል። ቤተ ፈት የምትባለው ባል አግብታ እየኖረች ከጊዜ በኋላ ባሏን ፈታ የኮበለለች ሴት ናት። ከሄደችም ችግር ሲያጋጥማት የሚታያት ባሏን መበደሏ ሳይሆን ከባሏ ጋር በምትኖርበት ጊዜ የነበራት ምቾት እና ክብር ነው። አባታችን አዳምን ግን የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም ማለትም ኃጢአት ሰርቶ ከገነት በተባረሩ ጊዜ ፈጣሪዬን አስቀየምኩት ስለ በደሉ ያለቅስ ነበር። እንደዚህ ሁሉ ሰው በልዩ ልዩ የዝሙት ኃጢአት በተሰነካከለ ጊዜ "ድንግል ነኝን?" "ተክሊል ይገባኛል?" እያለ ያወጣውና ያገኘውን እያሰበ ከመተከዝ" አንተን ብቻ በድልሁ በፊትህም ክፋትን አደረኩ መዝ 51፥4 ማለት ኃጥአቱን እያሰበ ቢያለቅስ በንስሐ አዳምን መስሎታልና የቤተ ፈት ፍቃድ ልማድ አላገኘውም ይባላል። በመጨረሻ ከማስተርቤሽን እና ይህንን ከመሰሉ የዝሙት ርኩሰት መንገዶች የምታመልጠው በተቀደሰው ጋብቻ አማካኝነት ነው። ይህንን በተመለከተ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል ፦ ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱም ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት። 1ኛ ወደ ቆሮንጦስ 7፥2 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ዝሙትን ጠንቅ ብሎ ነው የጠራው በወጣትነት ወራታችን ከዲያብሎስ ከሚወረወሩ ፈላጻ ለመመከት ጋሻ መሆኑን ከገጸ ንባቡ እንረዳለን። በእውነት ከሴጋ የኃጢአት ዓለም ወጥተን በተቀደሰ ጋብቻ ለመኖር ማሰባችን የሚመሰገን መንፈሳዊ ውሳኔ ቢሆንም ጋብቻችንን ግን በትህትና በተሰበረ ልብ ልንፈጽም መዘጋጀት ይኖርብናል። አንዳንድ ሰዎች ማስተርቤሽን ሲፈጽሙ ከኖሩ በኋላ የንስሐ አባቴ ፈቅደውልኛል በማለት ተክሊል ለመፈጸም ሲዳፈሩ ይታያል። እነዚህ ሰዎች ስለ ማስተርቤሽን በጥልቀት ለንስሐ አባታቸው ሳይናገሩ በሥጋ ብቻ ድንግል መሆናቸውን ብቻ አጉልተው በማምታታት በማድበስበስ ኑዛዜ ፈጽመው ወደ ተክሊል ለመምጣት የሚያደርጉት ጥረት ለምዓት ካልሆነ የበረከት መንገድ አለመሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነውና መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ተወዳጆች ሆይ ከድፍረት የሚገኝ ምንም አይነት መንፈሳዊ በረከት የለም። ድፍረት መንፈሳዊ ኪሳራን ለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊት እንደዚህ ያለው "የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባርያህን ጠብቀኝ ያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ" መዝሙር 19፥13 ምን አልባት አንዳንድ ካህናት ስለዚህ አይነት ኃጢአት ግንዛቤ ሳይኖራቸው ቀርቶ ተክሊል ፈጽሚ ተክሊል ፈጽም ቢሉን እንኳን ራሳችንን ዝቅ አድርገን አይገባኝም😔 ልንል ያስፈልጋል። በቀጣይ ክፍል በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን? የሚለውን ጥያቄ እንመለከታለን የዛሬው ጥያቄ የተመለሰላችሁ👍 በማድረግ ግለጹ @abrehamuslase
Dec 28, 2021