በ 26 አመት ከሚበልጠኝ ሰው ጋር ፍቅር ያዘኝ እሱን ለመተው ምላርግ? ሰላም ሰዎች በእድሜ በ26 አመት ከሚበልጠኝ ሰው ጋር እብድ ያለ ፍቅር ይዞኛል። ከዚህ በፊት የሚሰሙኝ የፍቅር ስሜቶች በጣም ያስጨንቁኝ ነበረ...ሆኖም እሱን ስወድ ግን ደስ እያለኝ ውስጤ ሰላም እየተሰማው ነው። እሱ ማለት ለእኔ ከእኔ በላይ እኔን የሚወደኝ ሰው ነው፣ ራሴን ላጠፋ ጫፍ ደርሼ ብዙ ጊዜ ውስን በሆኑ ቃላቶች ሀሳቤን የሚያስቀይረኝ ሰው ነው፣ለእኔ የውስጥ ክህሎቶቼ ምንም አይደሉም ለእሱ ግን ዋጋ አላቸው እኔ ያንን ክህሎቴን አውጥቼ የምጠቀምበትን መንገድ ያመቻችልኛል። እሱ ለእኔ ስሜት እንዳለው አውቃለሁ ግን ፍቅር ነው ብዬ አላስብም ...ከእሱ ስለመራቅ ብዙ ጊዜ አስባለሁ ግን ባሁኑ እየተሸነፍኩ ነው። እንደውም በቅርቡ ላገኘው ነው....😔 በሀይማኖት አንድ አደለንም በዚህ ላይ የእድሜው ነገር🙈🙈 እና ምን ትመክሩኛላችሁ ???
Dec 27, 2021ለማግኝት ትክክል አደለም ብለሽ ካሰብሽ ለምን ታግኝዋለሽ እንደ ምክንያት ያስቀመጥሻቸው ነገሮች ውስጥሽን የሚረብሹት ከሆነ ለምን መገናኝቱን እኮ ፍቃደኛ አደለሽም ስለዚህ እንደ እኔ እኔ አታግኝው ውስጥሽን አዳምጪ የሀገሬ ሰው ምን ይላል መሰለሽ ለተቀማጭ ሰማይ ቅርብ ነው ምን ልልሽ ፈልጌ መሰለሽ እኛ የተለያዮ ሀሳቦችን ልንነግርሽ እንችላለን ነገር ግን ራስሽን አዳምጪ ምክንያቱም የአንቺን ሂወት እኛ ልንኖረው ስለማንችል ትክክል ነው የምትይው ነገር አድርጊ ባይሆን ሰውየውን ቤተሰብ አድርጊው አንቺ የራስሽን ሂወት ጀምሪ if you get my answer useful can i get ✅ tnx
Dec 27, 2021