Orthodox yehonachu pls melsulg Betam gera selgebage nw ega sentemek be abe weld menfas kedus belen nw aydel lmn be eysus sem alhonem bible lay hultum selal nw ena sel selase meyawera bota kale bible west ngerug pls ena demo lmn maheteb enaseralen,sel seal adeno ngerug btw orthodox ng gn bezu malwkew nger ale sew betykg enkuan memels endchel ngerug sel seratu
Dec 25, 2021ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን በጌታችን በኢየሱስ ስም ሳይሆን በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም ሚስጥረ ጥምቀትን የምትፈጽመው ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ያጠምቁ ዘንድ ሐዋርያትን ስላዘዛቸው ነው። በአካል በስም በግብር ሶስት በመለኮት በስልጣን በአገዛዝ አንድ በመሆናቸው በሶስት ስም (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) በአንድ አምላክ( እግዚአብሔር ) ስም ጥምቀት ይፈጸማል። ከብዙ በጥቂቱ። የእግዚአብሔር አንድነትና ሶስትነት በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ዘፍ 1:26 ዘፍ 3:22 ዘፍ 11:7 ዘፍ 18:1-15 ኢሳ 6:1-3 ማቴ 3:16 ማቴ 28:19 ሉቃ 1:35 ዮሐ 14:25 1ቆሮ 12:3 2ቆሮ 13:14 እንደምሳሌ መመልከት ትችላለክ። ማዕተብ ዐተበ ከሚል የግዕዝ ቃል የወጣ ነው። ማዕተብ ስንል የተባረከ ይሆናል።በአንገታችን የምናስራቸው ክሮች ተባርከው ስለሆነ ማዕተብ ተብለው ይጠራሉ። ነጭ ቀይ ጥቁር ክር በአንድ ተገምደው ይታሰራል ይኽም አንድምታዊ ፍቺ አለው። በተመሳሳይ መልኩም ጥቁርም ክር እንደዛው። ማዕተብ ማሰር የተጀመረውም በያዕቆብ ዘእልበለረዳኢ ዘመን ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ከዚኽ በተያያዘ እንዲሁ ክታብም ይታሰራል።ሰኔ ጎሎጎታ ትምህርተ ኅቡአት ይጠቀሳሉ።ይኽም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ሥዕል በእግዚአብሔር ፊት የተሰጠ ሕግ ነው።ማንም ሰው ሥዕል መሳል ስለቻለ ብቻ እነዚኽን ቅዱሳት ስዕላት መስራት ይችላል ማለት አይደለም የራሳቸው ህግ አላቸው። የሰዓሊውምን መልካም የሆነ መንፈሳዊ ሕይወትን ያጠቃልላል። የአጠቃቀምም ስርዓት አላቸው። በዚህ አጋጣሚ በቲሸርት ላይ ቅዱሳት ሥዕላትን የምታሰሩ ሰዎች መልካም እያደረጋችሁ አይደለም። ትክክል አይደለም። ነገሩ ዝርዝር ቢሆንም በአጭሩ እንደ መግቢያ ይረዳካል።
Dec 26, 2021