ሰላም ውዶቼ እንዴት ናችሁልኝ ዛሬ ከተፍ ያልኩት አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ነው።ምን መሰላችሁ ብዙን ጊዜ በትምህርት ቤት ውስጥ ምናምን በጣም እየፈራው ተቸገርኩ፤አንዳንዴ ይሄ ፍርሃቴ በውስጤ ያለውን እምቅ ችሎታ እንዳላወጣ ጥብቅ አድርጎ ያስረኛል፤ሌላ ጊዜ ደግሞ ሴቶችን ሳይ የመፍራት እና አይናፋር የመሆን ችግር ያጋጥመኛል፤በተለይ በክፍል ውስጥ ክርክር ወይም ውይይት ሲኖር ከፍርሃቴ የተነሳ በራስ መተማመኔን አጣና የያስኳቸውን ሃሳቦች ባለመናገር ጊዜዬን አባክናለሁኝ፤ከዚህ ፍርሃቴ ለመውጣት ብዙ ሞክሬያለሁ ግን ሁሌ የሚያሸንፈኝ እሱ ነው።እና ከዚህ ፍርሃት ለመውጣት ምን ላድርግ የእናንተ ምክር ያስፈልገኛል
Dec 24, 2021በመጀመሪያ ፍርሀት ተፈጥሮዊ ነው።የትኛውንም ደፋር ነው የምትለውን ሰው ብትጠይቀው ሳይፈራ ቀርቶ አይደለም ግን ፍርሀቱን አሸንፎ ነው ደፋር የሆነው።ይህ እንዴት ይቻላል ካልከኝ ደግሞ የሚያስፈራህን ነገር ደጋግመህ በማድረግ ፊት ለፊት በመጋፈጥ ነው።ብዙ ጊዜ የሚያስፈራህን ነገር ደጋግመህ አድርገው።ለራስህ እኔ ደፋር ነኝ።እኔ በሰዎች ፊት ሀሳቤን የመግለፅ ብቃት አለኝ እያልክ ደጋግመህ ንገው።እንደምታደርገው ሙሉ እምነት አለኝ። @yordi677
Dec 24, 2021