አባቴ በወለዳቸው ልጆች በጣም ያፍራል ፣ ከእኛ በላይ የሚያስበው ገንዘብ ነው። ከሁሉም በላይ ገንዘብ ነው የሚያፈቅረው ፣ የሆነ ሀሳብ ስንጠይቀው ስናወያየው ገንዘብ የምንጠይቀው እየመሰለው ሁሌ ስድብ እና ጭቅጭቅ ነው። እናቴ በጣም ትለፋለች በተሰቡን የምታስተዳድረው እሷ ናት እሷ ሰርታ የምታመጣውን ገንዘብ ከግማሽ በላይ የምትሰጠው ለሱ ነው። ከዛ በተረፈው ገንዘብ የተሟላ ህይወት ታኖረናልች ፣ ግን እሱ ሁሌም ይሰድበናል ሁሌም ይጨቀጭቀናል። እናቴን ሁሌም የማፅናናት እና የማወያያት እኔ ነኝ ግን አሁን መረረኝ። እኔ ሰልችቶኝ ከቤት ልወጣ እያሰብኩ ነው ምን ትመክሩኛላችሁ ? በዛ ላይ የራሴ የምለው ህይወት እያስጠላኝ ነው ። ፍቅር የሌለበት ህይወት ስኖር ወደ 15 አመት አለፈኝ ከቀን ወደ ቀን ይስተካከላል ብየ አስብ ነበር በተለይ በዚህ 3 እና 4 አመት የአባቴ ሁኔታ አአስጠልቶኛል ግን ደግሞ እናቴ እና ታናሽ እህቴ ሁሌም ያሳስቡኛል ። ምን ትመክሩኛላችሁ
Dec 23, 2021Brother እኔም እንዳንተ አይነት ህይወት ነው የነበረኝ ታገስ ውጪ አንዴ ከወጣክ ምንም ሳትይዝ ህይወት ዘላለም ምስቅልቅል ነው የሚለው አንተ የሚገባክን አድርግ ተማር ሙያ ልመድ ብዙ ጊዜ እቤት አታሳልፍ ቢያንስ ትንሽ ነገር ከያዝክ ብትወጣም የመቀየር probability ይኖርካል ግን በፍፁም ጎዳና እንዳትወጣ በፍፁም እኔም ያሳለፍኩት ነው
Dec 23, 2021