Also #religious Hey hey guys Selam new eee Idk how to ask but I tnk u know about masterbation thing ... Dro maletma ke 6 or 4 months ago betam telekfe neber keza nsha gebche akomkugn completely keza kewer mnamn befit I got in rnsp and started to date .. keza behuala gn dro emichawitbgn Mendes kendegena tefetatenegn 3 ,4gixe adereku I really really felt guilty gn still kesua ga date Adrge simeles or movie say beka any dirty neger horny yadergegn ena endaderg yigefafagnal kaderekut behuala gn malkes new emiKeregn betam new emikochegn please religiously or somehow endet new kezik neger mewutat emchilew I mean like addicted hugnalew eyalku adelem gn even alfo alfo betam rarm bihon eyeteshenefku new Beka kehasabe endet adrge lawutaw guys please , ye orthodox priests mnamn kalachihu help!
Dec 21, 2021ከፈተና እንድናመልጥ ቅዱሳን አባቶቻችን ስድስት ደረጃዎችን አስቀምጠውልናል።የመጀመሪያዎቹ አራቱ አንዱ ሌላውን ተከትለው የሚመጡ ናቸው።የፈተና የመጀመሪያ ደረጃ ( Provocation (ነቅዓ ኃልዮ መነሳሳት)ሲሆን እሳቤው ወደ ኃጢያት መመልከት ዝንባሌ ነው። ኃጢያት በአሳብ በሥዕል መልክ በአይምሮአችን ይቀረጻል።ሀሳብን የትም ብትሄድ ማስቆም አትችልም መቃወም እንጂ።እዚህ ደረጃ ላይ ስትሆን የኃጢያት ዝንባሌ እንጂ በራሱ ኃጢያት አይደለም። ይህ በሀሳብ ደረጃ የተጸነሰ ኃጢያት ግን በተግባር ደረጃ ያድጋል።#ሀሳብ እንዳለ መቃወም ያለብክ ለዚህ ነው። እንዳያግ 1. ማማተብ 2. እግዚአብሔርን ማሰብ 3. ይኽን ክፉ ሀሳብ ያሳሰበክን ክፉ መንፈስ መገሰጽ። ከዚህ አያልፍም ነገር ግን ካለፈና ውጊያው ከበረታ 1. ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ላይ መሆን 2.በፍጹም በፍጹም ብልትን (እስኪትን) አለመንካት። ደግሜ እላለው። አለመንካት። መጻሕፍተ መነኮሳት ላይ እንዲህ ያለ ጾር በሚነሳበት ግዜ ዲያቢሎስ እስኪት ላይ ከፍተኛ የሆነ የማሳከክ ስሜትን እንደሚያነሳ የተገለጠ ሲሆን በዚኅ ግዜ በፍጹም አለማከክ አለመንካት። 3. ከዚኽ ከባሰ ፊትን ወደ ምስራቅ አዙሮ ቀራንዮን በማሰብ መንበርከክ። ዲያቢሎስ በ2 መንገድ ከፈጣሪ ያርቅካል አንደኛ ኃጢያት እንድትሰራ በመገፋፋት ሁለተኛ ኃጢያት ካሰራክ በኋላ እንድትጸጸት በማድረግ ተስፋ እንደሌለክ አድርጎ ያሳይካል ከንቱ ጸጸት። ስለሆነም ቢቻል ላለማድረግ መጣል ከወደቅክ ግን በኃጢያቱ ሳትውል ሳታድር ከመምህረ ንስሀ ዘንድ ቀርቦ ንስሀ መግባት።አንተ ንስሀ መግባት ይሰለችክ ይሆናል እግዚአብሔር ግን አንተን መማር ስለማይሰለቸው ሳታፍር ሄደክ ንስሀ ግባ። እማ አመላክ ትርዳክ ለሷ ደግሞ ንገራት። እንደዚህ አይነት ነገር እየተከታተላችሁ ግን የሰውን ደካማ ጎን በመመልከት ለመርዳት በሚመስል ሽሙንሙን ቃላት በሰው ላይ የምንፍቅናችሁን አተላ የምትረጩ የሉተር ቡችሎች ግን እግዚአብሔር አምላክ ይፋረዳችሁ።
Dec 22, 2021