ሀገራችን ኢትዮጵያን ለ6 ሠዓታት ብቻ የመሩት ቆንጅዬው መሪ እና በስልጣን ያልዘለቁበት እጅግ አስገራሚም፤ እጅግ አሳዛኝም ታሪክ ,,,
.
አፄ ገስዩ /Atse Gessiyou/ ይባላሉ፡፡ ከክ.ል.በ. በ665 ዓ.ዓ. የኢትዮጵያ 67ነኛው ንጉስ ሆነው የንግስና ዘውድን ይደፋሉ፡፡ ታዲያ በወቅቱ እንደነበረው ስርዐት የአካባቢው ሠዎች ለንጉሡ ሠላምታና ምስጋና ለማቅረብ ወደ ቤተ ዙፋናቸው ይሄዱ ጀመር፡፡ ከዛም በየተራ ለእሳቸው የክብር ምስጋና ማቅረብ እንደተጀመረ በቃላት ከሚገለፀው በላይ እጅግ በጣም ቆንጆ መሆናቸውን ያያሉ፡፡ ይገረማሉ፡፡ 'ይኼማ የፈጣሪ ተዓምር ነው' በማለትም ከፍ ባለ ድምፅ የአፄ ገስዩን ውበት ማሞገስ ይጀምራሉ፡፡ ይህ ወሬም በየአካባቢው ሁሉ ናኘ፡፡ በቃ የቤተ ዙፋኑ ጠባቂዎች ሊቋቋሙት ከሚችሉት በላይ ሠዉ ወደ አፄ ገስዩ ዙፋን መጉረፍ ጀመረ፡፡ ,,, እናማ ,,, በዚህ ሳቢያ በተፈጠረ ጭንቅንቅና ግፊያ ቆንጅዬው ኢትዮጵያዊ መሪ አፄ ገስዩ በነገሡ በ6 ሠዓት ውስጥ ተረጋግጠው ሞቱ፡፡ ,,, በእሳቸው ምትክም አፄ ኑአትሚአሙን /Atse Nuatmiamun/ 68ኛው ንጉስ ሆነው ተሾሙ፡፡ አስባችሁታል ይህ ታሪክ በግሩም መልኩ በፊልምና በዶክመንተሪ ቢሠራ ,,, !?
.
ምንጭ :-
የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ መፀሐፍ /ገፅ 80/
ደራሲ - አለቃ ታዬ
እንዲሁም ሌሎች ሁለት መፀሐፍት
Dec 18, 2021