Zetenu ye egziabher neus baelat eneman nachew ebakahu melsu any senbt temari kale its urgent
Dec 16, 2021ይቅርታ ከተሳሳትኩኝ 🙏🙏🙏 ንዑሳን በዓለት ንዑሳን በዓላት ማለት የክብራቸው አነስተኝነት መግለፅ ሳይሆን በሰዎች የበዓል አከባበር ከላይ ካየነው አነስተኝነቱን ለመግለፅ እንጂ ጌታ ከፈፀማቸው ሥራዎች ማበላለጥ ሆኖ አይደለም 1⃣. በዓለ መስቀል ቀኑ፡- መስከረም 17 በዓሉ፡- ንግስት እሌኒ የተባለች ጻድቅ መስቀሉን ከተቀበረበት ለማውጣት ያስቆፈረችበት እና ያወጣችበት ይታሰባል መስቀሉ የወጣው መጋቢት 10 ሲሆን በአብይ ፆም ምክንያት ቁፋሮ በተጀመረበት እና መስቀሉ የተገኘበት መስከረም 17 በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር ቤተክርስቲያን ወስናለች 2⃣.ስብከት ቀኑ፡- የልደት ሳምንት ሲሆን ፆም በገባ 4ኛ እሁድ ላይ ይውላል በዓሉ፡- ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል እያሉ ያስተማሩበት ይህ ትምህርታቸው በክርስቶስ እውን እንደሆነ የምናስብበት ነው ዮሐ.1፥44 3⃣.ብርሃን ቀኑ፡- የልደት ሳምንት ሲሆን ፆሙ በገባ በ5ኛው እሁድ ይውላል በዓሉ፡- ነብያት ይወርዳል ይወለዳል ያሉት ብርሃን እንደሆነ በጨለማ ለሄዱት ብርሃኑን እንደገለፀላቸው ያመለክታል ዮሐ.1፥1-19 4⃣.ኖላዊ ቀኑ፡- የልደት ሳምንት ሲሆን ፆሙ በገባ በ6ኛው ሳምንት ወይም ልደት ከመከበሩ በፊት ያለው እሁድ ላይ ይውላል በዓሉ፡- ነብያት ይወርዳል ይወለዳል ያሉት ክርስቶስ መልካም እረኛ እንደሆነ እና ለተቅበዘበዙት ዕረፍት የሆናቸው እሱ ስለ መሆኑ የሚገልፅ ነው ዮሐ.10፥1-22 5⃣. ግዝረት ቀኑ፡- ጥር 6 ቀን ይውላል በዓሉ፡- በተወለደ በ8ኛው ቀን ሊገረዝ መሄዱን የሚያመለክት በዓል ነው ስሙም ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ ሉቃ.2፥21 6⃣.ልደተ ስምዖን ቀን፡- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ በ40 ቀኑ የሚከበር በዓል ነው፡፡ በዓሉ፡- አረጋዊ ስምዖን ጌታን አቅፎ ትንቢት እንደተናገረ በሙሴ የተነገሩት ሁሉ እንደተፈፀሙ ይተርካል ሉቃ.2፥25-35 7⃣.ቃና ዘገሊላ ቀኑ፡- የካቲት 23 በዓልን ከበዓል ጋር በማገናኘት የሚከበረው ጥር 12 ተደርጓል በዓሉ፡- በቃና ዘገሊላ የመጀመሪያ ተአምር የተደረገበት እና ክብሩ የተገለፀበትን ይታሰባል ዮሐ.2፡1-12 8⃣. ደብረ ዘይት ቀኑ፡- የአብይ ፆም እኩሌታ ሲሆን እሁድ ላይ ይውላል በዓሉ፡- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ስለ መምጣቱ ያስተማረበት እና ስለ ዓለም ማለፍ የተናገረበት ነው፡፡ ማቴ. 24፥1 9⃣ኛ በዓለ ድህነት
Dec 16, 2021