ሰዎችዬ እናት ማለት ትርጉሙን አውቀዋለሁ።ግን የኛ እናት አራት ልጆች ወልዳ ሁለቱን ብቻ ልጆቿ አድርጋ የምታስብናየምትወድ ሁለታችንን ደግሞ ከትንሽነታችን ጀምራ ለይታ የምትጠላንና የምትጨቁነን ናት።በዛም እኔና አንዷ እህቴ የአእምሮ ህክምና ደረጃ ደርሰናል።ጭራሽ እኔን ከአንጀቷ እንዳስወጣችኝና ልጇ እንዳልሆንኩ ነግራኛለች።ነገሩ እኔንም ቢያመኝም ከኔ ይበልጥ በጭካኔዋ የምትጎዳው እህቴ ሁኔታ አሳስቦኛል።እህቴ ሶስት ትናንሽ ልጆች ያሏት ስትሆን አንዷ ልጇ ኦቲዝም ስላለባት በዛም የምትሰቃየው ሳያንስ እናት ተብዬዋ ለይታ ከምትወዳቸው ልጆቿ ጋር እሷን በጭካኔ የምትጎዳት ሆናለች።ምን ባደርግ ትመክሩኛላችሁ?አሁን ላይ ስራ የለኝም።የስነልቦና ህክምና ከአንዴም ሁለቴ ሞክሬ በዚህቹ ሴትዮ የማያባራ ጥቃት ከሽፎብኛል።እህቴም ካበደች ሶስቱ ህፃናት ልጆቿ ካለአሳዳጊ እናት መቅረታቸው ነው ምን ላድርግ? እባካችሁ መላ ፈልጉልኝ
Dec 15, 2021😭 ፈጣሪ ልቦና ይስጣት ። ነገር ግን እናንተን ለይታ ምትጠላበት ግልፅ ምክንያት ካለ እሱን ማሻሻል ነው ። ሌላ ደሞ ሁኔታውን ለምትወዳቸው እህትነሰ ወንድሞቻችሁ በማስረዳት እነሱ መሃል ገብተው ፀባያቸውን እንዲያሻሽሉ ቢመክሯቸው እነሱን ስሚወዱ ሊሻሻሉ ይችላሉ ።
Dec 15, 2021