ሁለቱ መላጦች ============= ሁለት በራ ሠዎች ሲያልፉ በጎዳና ዕቃ መሬት ወድቆ ብልጭ ሲል ያዩና ተሽቀዳድመው ሄደው ከቦታው ሲደርሱ ተፎካከሩበት ሁለቱም ሊያነሱ። በኀላም ተማተው በጥፊ በጡጫ አንደኛው ነጠቀ በጉልበቱ ብልጫ አገላበጠና ቢመለከት ፈጥኖ ዕቃውን አገኘው ማበጠሪያ ሆኖ። እስኪ ሁላችሁም በሉ ፍረዱት እሱ ራሱ በራ ፀጉር የለበት ሮጦ ተማቶ ቀምቶ ቢያመጣ ምን ያደርግለታል ሚዶ ለመላጣ? ሰዎች ይፋጃሉ አስበው ሳይፈርዱ የተጣሉበትን ጥቅሙን ሣይረዱ ከመጣላት በፊት ከመቀያየም የነገሩን ፍሬ መረዳት መልካም። ---------------------------- @GORO_LIBRARY_BOT
Dec 12, 2021