•የድቁና ማዕረግ (ክህነት) በጳጳስ አንብሮተ ዕድ የሚሰጥ ዝቅተኛው የክህነት ደረጃ ነው፡፡ ተግባሩም በቤተ ክርስትያን አገልግሎት መፋጠን እና መታዘዝ ነው፡፡ •የቅስና ስልጣነ ክህነት ደግሞ ሁለተኛው ደረጃ ሲሆን ከራሱ ከመድህንዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠውን ቃል ማለትም ’’ በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል ” ብሎ ስልጣንን ለሐዋርያት የሰጣቸውን አሁንም አባቶቻችን ከሐዋርያት የተቀበሉት ስልጣን ነው፡፡ •መሪጌታ ደግሞ ለረዥም አመታት ቃለ እግዚአብሔርን በየጉባዔ ቤቱ የተማሩ እና አንዱን መርጠዉ ደግሞ የሚመረቁበት ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ መሪጌታ በሁሉም ጉባዔ ቤቶች ገብቶ ከተማረ በኋላ ለምሳሌ ቅኔ ቤት፣ አቋቋም ቤት፣ ድጓ ፣ ዝማሬ መዋሲት ከተማረ በኋላ በአንዱ ድግሞ ለምሳሌ በቅኔ ራሱን አብቅቶ የቅኔ ሊቅ ወይንም መምህር መሆን ይችላል ያኔ መሪጌታ ሆነ ማለት ነው፡፡
Dec 11, 2021