I'm protestant...it's when he turned water into wine at a wedding
Dec 10, 2021I'm protestant...it's when he turned water into wine at a wedding
Dec 10, 2021ፕሮቴስታንት እና ካቶሊኮች ምላሻችሁ ጥሩ ነው ከምታውቁት ነው የተነሳችሁት ከ30 ዓመቱ ጀምሮ ያለውን ተአምር ነው የምትጠቅሱት መልካም ነው እንዳለ መታደል ሆኖ ከእናቱ ማህጸን ጀምሮ እናንተ እስከጠቀሳችሁበት ግዜ ድረስ የነበረውን እድገቱን ተግባሩን አታዉቁም በቤተ መቅድስ ከመጥፋቱ በቀር።ያሳዝናል ምን ሲሰራ ኖረ ከህጻናቱ ጋር በምን መልኩ አደገ ምን ምን የሚሉትን የምታውቀው የመመለሱም አቅም ያላት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ብቻ ናት። አይ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የለም ካላችሁን ደግሞ አምጡ አስተዳደጉን . . . . ለማንኛውም እህቴ ለጥያቄሽ ምላሽ ግን እንደሚከተለው እላለው። ወልደ አብ ወልደ ማርያም ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኔዓለም ተአምሩ የሚጀምረው #ከመጸነሱ ነው።ሰማይና ምድር የማይችሉት አምላክ ምሉዕ በኩለኼ የሆነ የዓለማት አስገኚ በ15ዓመት ብላቴና ማህጸን ውስጥ ማደሩ ተዓምር ነው።🙆♂ አምላክን በወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ሕሊና ሕትምት በምትሆን በእመቤታችን በማርያም ማህጸን በተጸነሰ ግዜ አካላዊ ቃል የእመቤታችንን መልክ ይለውጠው ነበር ለዚኽም ዮሴፍ አያውቃትም ነበር እንደ ሮማን አበባ የምትነጣበት እንደ ጽጌሬዳም የምትቀላበት ግዜ ነበር ከወለደችው በኋላ ግን መልኩ ስላልተለዋወጠ ዮሴፍ አውቋት ነበር።ድንቅ ተአምር ነው🙆♂ በበረት መወለዱ በጨርቅ መጠቅለሉ ይኽ ሁሉ ተአምር ነው ከዚባሻገር አእዋፋትን በጭቃ እየሰራ ያበር ነበር በጨረር እየተንሸራተተ ቢጫወት እሱን ተመልክተው ህጻናቱ እንደሱ ለመጫወት ቢወጡ እየወደቁ ሞተዋል በዚኽም ወላጆቻቸው ልጆቻችንን ገደልክ ቢሉም የሞቱት ተነስተው ድንቅ ድንቅ ምስክርነትን ሰጥተው ዳግም አርፈዋል እናቱ ይማር ዘንድ ከመምህር ብትልከው የመምህሩን ቀለም ቢደባልቅ መምህሩ ቢቆጣው የተደባለቁትን ቀለማት ለይቷል ኽረ ስንቱ እህቴ ስራው ብዙ የኛ ጌታ እንደተወለደ የ30 ዓመት መሆን ሲችል ጥቂት በጥቂት በማደጉ ውስጥ ብዙ ተአምራት አሉ። እመቤታችን በዚህ ሁሉ ግዜ አብራው በመሆኗ በሷ ልቦና የተቀመጠውማ ምን ይረቅ ምን ይደንቅ። ተአምረ ኢየሱስ ማግኘት ከቻልሽ እዛም ላይ ተመልከች።
Dec 20, 2021Not only for ortho but 4 all Christians kana zegelila lay wihan wede weyn tej keyere that is his first miracle😊😊
Dec 12, 2021