ይህ ያለስጋት መጠየቅ የምችልበት ስለመሰለኝ እዚህ መጣሁ፣ እኔ ሀገሬን እወዳለሁ ፣ ጦርነትን አልወድም፣ እናም ወደ ጥያቄዬ ስገባ በየቦታው እየተፈተሽን እና መታወቂያ እያሳየን እንገኛለን ይህም ደስ ይላል፣ ምክንያቱም ለራሳችን ሰላም ነው። ግን ይህንን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ከአ.አ መውጫ ላይ በተለይ ስምን በማንበብ ሰውን ያንገላታሉ። ለምሳሌ እኔ ብሔሬ ጉራጌ ሲሆን የአባቴ ስም ገብረስላሴ ነው እናም በስሜ ምክንያት ሁለት ጊዜ ችግር ገጠመኝ፣ ከትላንት ወዲያም የትግሬ ስም ነው ትግሬ ነህ አለኝ፣ እኔም ገርሞኝ ሀይሌ ገብረስላሴ ትግሬ ነው እንዴ አልኩት። አንተ ሂድ መታወቂያህን ግን ይዘዋለሁ ብሎ ሸኘኝ፣ ምን ማለት ነው? ምንም አይነት ችግር ሳይኖርብኝ በአባቴ ስም ምክንያት ከቤት መውጣት አልቻልኩም? ምን ባደርግ ይሻላል?
Dec 06, 2021Similar with me y grandfather name hagos nw ene behere amhar gn bzhe semi mikiyate bzu gize tesekayechalhu 😭😭😭😭😓😓😓😓😓😓😓
Dec 06, 2021