What are your depressions guys? Mine is , i have this sub concsious mind i can't control . It just kept on cursing God and i kept on being depressed . It is hard to curse God .. What about you Guys , at least , let's confess Anonimously . I think those who are close to us like to laugh at us .. They are less likely to feel us.
Sep 05, 2019የአየር አጋንንት በልባችን አድሮ እግዚአብሔርንና ቅዱሳኑን ይሳደባል /ብዙ ወንዶሞቼና እህቶቼ የሚሰቃዩበት ፈተና/ በቀሲስ መ/ር ሄኖክ ወ/ማርያም ✝ ✝ @kegdlat ተወዳጆች ሆይ ከግሸን ማርያም ተመልሼ ተከታታይ ትምህርታችንን እስክንቀጥል ‹‹የአየር አጋንንት ውጊያ በጸሎት ጊዜ›› ከሚለው አዲሱ መጽሐፍ ለቅምሻ እንድታነቧት ይቺን በግሸንዋ ማርያም ስም ዘክርያቹኃለሁ፡፡ ✝ @kegdlat የአየር አጋንንት እና ሌሎቹም ርኩሳን መናፍት በውስጣችን ከገቡ ግራ እስኪገባን ድረስ ቅዱሳንን ይሳደባሉ፡፡ እስኪ ብዙዎቻችንን የምንቸገርበት የራሳችን ሐሳብ እስኪመስለን የምንሰቃይበትን የአጋንንቱን የፈተና ስልት እንመልከት፡፡ አጋንንት በጌታ ሰው መሆን ወይም ሥጋ መልበስ ላይ መጠራጠር የሳድርብሃል፡፡ ሰው መሆኑም እውነት እንዳይመስልህ ያደርግሃል፡፡ ✝ @kegdlat እመቤታችንን ‹እውን በድንግልና ነው የወለደችው›› ብሎ ጥርጥር ያጭርብሃል፡፡ ልትቆጣጠረው በማትችለው ሐሳብ ከውስጥህ ሆኖ እግዚአብሔርን ይሳደባል አንተም ይህ ውስጣዊ የአጋንንት ስድብ ካንተ ወይም እራስህ ከልብህ አመንጭተህ የተሳደብክ ይመስልህና ከመጨነቅህ የተነሳ ድንግጥ ትላለህ፡፡ አንዳንዱ በድጋጤ ድርቅ ይላል፡፡ ✝ @kegdlat በእመቤታችን ላይ ከውስጥህ ጸያፍ ነገር የሚናገር ድምጽ ትሰማለህ፣ቅዱሳንን አፍ ባያወጣም ከውስጥ ሲሳደብ ትሰማለህ፣ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የማይሆን ነገር በማሳሰብና የሚያስደነግጥህ ነገር ከውስጥ ሲናገር ትሰማለህ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን አትደናገጥ ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ ‹‹ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው›› በማለት አጋንንት በፈጣሪና በቅዱሳኖቹ ላይ የስድብን አፍ እንደሚከፍት ተጽፏል /ራዕ 13÷5/ ✝ @kegdlat ስድቡ ያናንተ ስላልሆነ እንዳትጨቅ፣ ነፍስህም ከእግዚአብሔር አንድነት የምትለይ አይደለችምና አትጎዳም፡፡ ሰይጣን ከውስጥ ሲሳደብ ነፍስ ትሰማለች ያኔም ትጨነቃለች ትደነግጣለች፡፡ ወዳጄ ነፍስ ፈጣሪዋን ስለምታውቅ ፈጣሪን አትሳደብም፡፡ ስድብ ቀድሞም ከነፍስ የተገኘ አይደለም፣ነፍስ ለዚህ ዓይነት ግብር አልተፈጠረችምና፡፡ ግን ስድቡን በውስጥ ሆኖ የሚናገረው የአየር አጋንንት እና ሌሎች ርኩሳን መናፍስት ናቸው፡፡ ✝ @kegdlat ሰይጣን ወደ እኛ ሕሊናና ልቦና ቀርቦ ይሳደባል፡፡ ያኔ ነው ስድቡ ከአንደበታችን ሳይወጣ በውስጥ የምነሰማው፡፡ በርትተን ከጸለይን እየመጣ ስድቡን የሚተነፍስብንን ስለሚተው እኛም ወደ ንጽሐ ጠባያችን እንመለሳለን፡፡ ወዳጄ ሰይጣን ወደ ሕሊናህ ቀርቦ ሲሳደብ ብትሰማ አንዲት ቃል አትናገር አትማረር ይልቁንም ‹‹ይህ ሐሳብ ያንተ ነው›› በለው፡፡ ሐሳቡ የእሱ እንደሆነ ከነገርከው ሥራውን ያውቃልና ይደነግጣል፡፡ አጋንንቱ ከሰው ጋር እያወራህ ድንገት በውስጥህ እግዚአብሔርን፣ ቅዱሳንን ሰድቦ ሊያስደነግጥህንና ትኩረትህን ሊያሳጣህ ይችላል፡፡ ✝@kegdlat ያኔም ‹‹ይህ ሐሳብ ያንተ ነው በለው›› ወዳጄ ሰይጣን የሕሊናውን ያውቃልና ስትነግረው ይሰማል በዛም ያፍራል፡፡ መቼም ‹‹ስነግረው እንዴት ይሰማል?›› ትል ይሆናል፡፡ ባንተ ያደረች ላንተ የተሰጠች ጸጋ እግዚአብሔር ታሰማዋለች፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ያሳፍርህ›› በለው፡፡ ሰይጣናት በክፉና ባልባሌ ሐሳብ የሚፈትናችሁ ከሆነ አትጨነቁ፡፡ ሰይጣን ልብ ውስጥ ሆኖ ለመሳደብ የዝሙት አጋንንትም ድረሻው ላቅ ያለ ነው፡፡ ፍትወትን በዓይነ ሥጋ እያሳየ የሚያሰቃየን አጋንንት ለስድብ ሰይጣናዊ ምላሱን መዘርጋት አይከብደውም፡፡ ✝ @kegdlat በጸሎት ሰዓት የስድብ ናዳ ከልቡ ጓዳ እያመጣ ሲጭንብህ እራስህ እንዳይመስልህ፡፡ ሰይጣን ነውና፡፡ ነፍስም የሷ መስሏት ትጨነቃለች፡፡ ወዳጄ እንደዚህ ያለን ጽኑ ስድብ አንተ/ቺ/ እንኳን የፈጠራችሁን እግዚአብሔርን ቀርቶ የምታውቁትን ሰው አትሰድቡም፡፡ ‹‹ማረኝ፣ ይቅር በለኝ፣ መንግሥትህን አትንሳኝ›› እያለች የምትጸልይ ነፍስ እንዴት ትሳደባለች? ነገር ግን የዚያ የርጉም ሰይጣንን ስድብ ሰምታ ጭንቅ ይሆንባታል እንጂ፡፡ ✝ @kegdlat ሰይጣን በሕሊናችን በጸሎት ሰዓት ስለሚሳደብ እኛ የተሳደብን የሚመስለን ለምንድነው? ካልን ከውስጥ ከሚወጣ ምስጋና ጋር ስድብ ስለሚወጣ ነው ከራሳችን የሚመስለን፡፡ ነገር ግን ምስጋናችን ከሰይጣን ስድብ ጋር አይቆጠርም፡፡ እኛ ፈጣሪ ፊት የቆምነው ለስድብ ሳይሆን ለምስጋናና ለጸሎት እንደሆነ ፈጣሪ ያውቃልና፡፡ ✝ @kegdlat እግዚአብሔርን የምትወድ ነፍስ ስለያዝክ የሰይጣንን ስድብ እየናቅህ አመስግን፡፡ ያማረ የተወደደ ምስጋናህን ከከዳተኛና ከተሳዳቢ ከሰይጣን ለይቶ የሚያውቅ አምላክ ነው ያለህ፡፡ ምንም የሰይጣን ስድቡ ካንተ ምስጋናና ጸሎት ጋር አንድ የሆነ ቢመስልህም ምስጋናዎችህ በእግዚአብሔር ዘንድ ከስድቡ ጋር አንድነት ስለሌላቸው ንጹሐን ናቸው፡፡ ✝ @kegdlat ወደጄ ሰይጣንን እራሱ ውስጥህ ሆኖ ይሳደብና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጠቅሶልህ ‹‹መንፈስ ቅዱስን የሰደበ ኃጢአቱ አይሰረይለትም›› እያለ ይሞግትኃል ያስጨንቅኃል፡፡ ሰይጣን ይህንን ኃይለ ቃል፣ ብዙዎችን ለማታለል ተጠቅሞበታል፡፡ ‹‹መንፈስ ቅዱስን የሰደበ›› ማለት መንፈስ ቅዱስ ሕፁፅ ያለ፣ ከሦስቱ አካላት አንዱ አይደለም ብሎ የካደ ኃጢአቱ አይሰረይም ማለት ነው፡፡ / ማቴ 12÷31/ ስለዚህ የሰይጣንን ስድብ በውስጥህ ተቃቀመው እንጂ ‹እኔ ነኝ፣ እግዚአብሔር ቢቀስፈኝስ፣ ጸሎቴን አይሰማኝም›› እያልክ ነፍስህን አታስጨንቃት ነፍሳዊ ሰላሟንም አታሳጠት፡፡ ይህ ፈተና ያንተ ብቻ ሳይሆን የአብዛኛው ምዕመናን ፈተና ስለሆን ሐሳቡን አታዳምጥ ተቃወመው፡፡ ✝ @kegdlat ሼር በማድረግ በዚህ ችግር ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ድረሱላቸው፡፡ 19/1/11 ዓ.ም ከግሸን ማርያም ከመስቀሉ ቦታ! @kegdlat @kegdlat @kegdlat
Sep 05, 2019