ሰላም ሰዎች ✌️ እኔ በራሴ አንድ ደስ የሚል ባህሪ አለኝ። ግን ሰዎች በሌላ ነገር ነው የሚተረጉሙት..... አንድ ወቅት ላይ የማልቀርባቸው ግን የማውቃቸውን ፣ ጓደኞቼ የሆኑ...ሰዎች ድንገት ሳላስበው የህይወት አጋጣሚዎች ብዙ ካራራቁን እነሱን ለማግኘት፣ ለማውራት ፣ለመሰብሰብ ጥረት አደርጋለሁ በዚህን ወቅት ሴቶቹ ጭራሽ ለእኔ ግድ አይሰጣቸውም። ወንዶቹ ደግሞ እኔን እንደ መጫወቻቸው ነው የሚያዩኝ (ጊዜ ማሳለፊያ) እነዚህ ሰዎች የሆነ ሰዓት እኔን እንደ ታናሽ እህታቸው ፣ ጓደኛቸው ነው የሚያዩኝ ይገባኛል ህይወት ለውጧቸው ይሆናል። ግን ቢሆንስ ወዳጅነታችን ጓደኝነታችን እንዲህ እንደቀልድ ዛሬ ላይ ይረሳል? ይረክሳል ወይ? የሚገርመው እነሱ ያን ማሰባቸውን ይሁን ብዬ ስቀበል ጭራሽ እኔም ያንን እንደፈልግ ነው የሚያስቡት...😒 እኔ ከትላንት የተለየ ማንነት የለኝም። እነሱ ግን ፊታቸውን ቢያዞሩብኝም ፤ ያለንን ጓደኝነት ወዳጅነት ጭራሽ በማላስበው፤ ፍፁም በእኔ በኩል በማይፈጠረው ግንኙነት ውስጥ ቢጥሉትም .....ለእኔ የነሱን ጓደኝነት ምንም አይለውጠው አይቀይረው። እነሱን ፈጣሪ ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ። አሁንም በጣም ነው የምወዳቸው...እና ግን እናንተ ምን ትመክሩኛላችሁ እኔ የድሮ ጓደኛዬን ካገኘሁ እንዳለየው ማለፍ አልችልም ስቀርበው ደግሞ ከላይ የፃፍኩትን አይነት ሰው ይሆንብኛል...ምን ሀሳብ አላችሁ?
Dec 03, 2021Just ignore them,,,they don't deserve your love and respect
Dec 03, 2021