ጥያቄው ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ነው ከልጅነቴ ጀምሮ ግራ የሚገባኝ ነገር አለ ባለፈው የሆነ መምህር እየሱስ ማእበሉን ፀጥ ያስባለው ለሙሴ በሃርን የከፈለለት አምላኩ መሆኑን ለማሳየት ነው ሲል ሰማሁ እና ደግሞ አባታችን ሆይ ላይ የእመቤታችን ስንቀጥል "የአሸናፊ የእግዚያብሄር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል" እንላለን እግዚያብሄር ደግሞ "የምወደው ልጄ ይሄ ነው እሱን ስሙት" እንዳለ መፅሀፍ ቅዱስ ይነግረናል ከዛ ሌላ ደግሞ እየሱስ በመስቀሉ ላይ "አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያቁምና ይቅር በላቸው" ብሏል እና በጣም ግራ እዠተጋባሁ ነው አና ጥያቄዬ በእግዚያብሄር እና በእየሱስ መሀል ልዩነት አለ ወይስ የለም? እባካችሁ በደንብ ብታብራሩልኝ ደስ ይለኛል
Dec 01, 2021ምስጢረ ስላሴ --------------------------✝✝✝✝ በዚህ እርእስ ትምርታችንን ስንጀምር የምናነሳው የምንማረው ስለ አለማት ፈጣሪ ስለ ቅዱስ እግዚብሔር የምንማርበት ክፍል ነው አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ለፍጡራኖቹ በተለይ ለሰውልጅ የተገለጠበት መገለጥ #ሃይማኖት ይባላል ይህንን መገለጥ አሜን ብለን ስንቀበል እምነት ይባላል ስለዚህ ፈጣሪያችን ቅዱስ እግዚአብሔር በቀጥታ እራሱን በገለጠባት ህጸጽ(ነውር) አልባ ውስጥ ሆነን አምላካችንን እራሱ ለአእምሯችን በሚመጥን መልኩ የተገለጠበትን በመመርመር ሳይሆን በወደደው መጠን በተገለጠበት መጠን አእምሮን በሚመጥን ሁኔታ የምናውቅበት መንገድ(ሃይማኖት) ነው። ይህም መንገድ ከመሰለ ነገር ግን መንገድ ያልሆነ በር የመሰለ ነገር ግን ገደል የሆነ ሜዳ የመሰለ ነገርግን አፋፍ ከሆነ እራሳችንን መጠበቅ የሰው ንቃተ ህሊናም ጭምር ነው። አምላካችንን ቅዱስ እግዚአብሔርንም ምንምኳ ፍጡር ሆነን ሙሉ በሙሉ ማወቅ መረዳት የማይቻለን ሲሆን ፈጽሞ አልተሰወረንም የምናውቀውን ያክል #እናውቀዋለን ይህም አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር #በ3 ዋና ዋና ጊዚያቶች ለሰው ልጅ በሚፈቅደው ሁኔታ ተገልጦ እንመለከታለን ማለትም 1.በህገ-ልቡና :-ይህ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ማንም ኦሪትን እና ወንጌልን ሳያስተምር ከአዳም እስከ ሊቀ-ነቢያት ሙሴ በልበ ሰሌዳቸው በህሊናቸው ተቀርጾ ይኖር ነበር 2.በህገ-ኦሪት :-ይህ ጊዜ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ከሊቀ ነቢያት ሙሴ ጀምሮ እስከ መጥምቁ ዮሐንስ እና እራሱ ባለቤቱ ክርስቶስ በስጋ እስከ ተገለጠበት ድረስ 3.በህገ-ወንጌል :- ይህ ጊዜ ደግሞ አምላካችን እራሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ከሰማያት ሰማይ ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማሪያም ተወልዶ አስተምሮ ሞቶ ተነስቶ አርጎ ደግሞ ዳግም እስኪመጣ ያለውን ጊዜ ያጠቃልላል እንግዲህ ከላይ እንዳየነው በእነዚህ በ3ጊዚያቶች ፈጣሪያችን ለፍጡራን የተገለጠበት መንገድ(ሃይማኖት) እናያለን “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ #በመንገድ #ላይ #ቁሙ #ተመልከቱም፥ #የቀደመችውንም #መንገድ #ጠይቁ፤ #መልካሚቱ #መንገድ ወዴት እንደ ሆነች #እወቁ፥ በእርስዋም ላይ #ሂዱ፥ #ለነፍሳችሁም👈 ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን፦ #አንሄድባትም👈አሉ።” — ኤርምያስ 6፥16 በዚች ቀጥተኛ መንገድ አልሔድም ያለ ሰው በር ወደ መሰለ ገደል መሔዱ አይቀርም አልሔድምም ካለ አይልፋ መንገዱን ያለጥርጥር በእርግጠኝነት #ስቷል መንገዱም እራሱ አምላካችን ነው። “ኢየሱስም፦ እኔ #መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” — ዮሐንስ 14፥6 በዚች ላይ እንጂ በፍልስፍና በተራታተረት የሚገኝ መንገድ የለምና 2ኛጴጥሮስ1:16 የቀደመች የተባለች===መጀመሪያ ኦርቶ=====ቀጥተኛ ዶክስ=====መንገድ ተዋህዶ ===እ/ር ሰውሆነዮሐ1:1 በዚች ድንኳን,ቤተ-መቅደስ,ቤተ-ክርስቲያን ሆነን ነው የአምላካችንን መገለጥ የምንረዳው *ስለዚህ ሥላሴን ባጭሩ #በሐካል ሦስት #በመለኮት ደሞ አንድ የሆነ አምላካችንን የምንረዳበት ምስጢር ነው ምስጢረ-ሥላሴ ። ሁላችንም እንደምናውቀው ሦሰትነታቸውን 1.በአካል 2.በስም 3.በግብር 4.በኩነት አንድነቱን ደሞ 1.በመፍጠር 2.በፈቃድ 3.በእዘዝ በአገዛዝ 4.ይህን አለም ፈጥሮ በማሳለፍ . . . #ስላሴ ሲባል በህሊናችን ሶሰትነቱን ብቻ የምናስብ አለን ያ ግን ስህተት ነው በሦስትነት ውስጥ ያለውንም ልዩ አንድነትም አለ። የሥላሴ ትምህርት ስናይ በጥቅሉ ባንድነት ውስጥ ያለ ልዩ ሦስትነት ነው። ይህን ስንል አምላካዊ እስትንፋስ ያለበት መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት በማድረግ ነው 👉ለምሳሌ “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን #ፈጠረ።” — ዘፍጥረት 1፥1 አባቶቻችን ነቢያት መፅሐፍ ቅዱስን ከቋንቋ ቋንቋ ከዘመን ወደ ዘመን ተርጉመውና አሸጋግረው እኛላይ አድርሰዋል ምስጋናም ይድረሳቸው ። ከአባቶቻችን ከነቢያት ሊቀ ነቢያት ሙሴ በኦሪት ዘልደት(ዘፍጥረት) መጽሐፍ ሲጀምር እግዚአብሔር ሲል በእብራዊያን ቋንቋ #ኤሎሒም በማለት ጠርቶታል ይህም ከአንድ በላይ ያለን ቁጥር ያሳያል አባቶቻችን ተቀብለው በሐገረኛ ቋንቋ ማለትም #በግእዝ እግዚአብሔር የሚለውን እንዲህ ገለፁ እግዚ---------ጌታ ኢየሱስ(ወልድ) አብ---------እግዚአብሔር አብ ሔር--------መንፈስ ቅዱስ ባጠቃለይም #እግዚአብሔር የሚለው ቃል የሶሰቱም የአንድነት መጠሪያ ስማቸው ነው ስለዚህ እግዚአብሔርንም በጠራን ጊዜ አብ,ወልድ,መንፈስ ቅዱስንም መጥራታችን ነው። አንዳንዶች ለ አብ ብቻ የሚሰጡ አሉ ስህተታቸውን ከነ መረጃ ይዘን እንመጣለን በቀጣዩ ክፍል ክብር ምስጋና ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሜን። @Orthodoxtewahdohaymanot21 @Orthodoxtewahdohaymanot21
Dec 01, 2021