bewerk neber mitashew makew ahun gin dermatology moltual mokir eski
Nov 23, 2021bewerk neber mitashew makew ahun gin dermatology moltual mokir eski
Nov 23, 2021Doctor Alle 8809/ዶክተር አለ 8809: ✍#ላሽ #በምን #ምክንያት #ይመጣል? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #ላሽ የተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅማችን ፀጉር የሚሰሩ ሕዋሳትን (hair follicles) በድንገት በማጥቃት የሚከት በሽታ ነው፡፡ ጥቃቱ በምን ምክንያት እንደሚከሰት ሳይንስ እስካሁን ያልደረሰበት ቢሆንም በመላው አለም በዚህ በሽታ በ10 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ይጠቃሉ፡፡ ⏩ #ላሽ በአንድ በተወሰነ ቦታ ላይ የፀጉር መርገፍ ሲሆን ቦታው የራስ ቅል፣ቅንድብ፣የአይን ሽፋሽፍት ወይም ፂም ሊሆን ይችላል፡፡አልፎ አልፎም በደረት በብብትና በብልት አካባቢ ያሉ ፀጉሮችን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ላሽ ከሰው ወደ ሰው አይተላለፍም፡፡ ⏩ #የበሽታዉ መንስኤ ምንድን ነዉ? 🔹 ህፃናት ላይ የሚታየው የራስ ፀጉር መመለጥ ምክንያቱ የፈንገስ ኢንፌክሽን ወይም ቆሮቆር ሲሆን ይሄም ከታከመ ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል:: 🔹 ህፃናት ላይ በአደጋ ወይም በእሳት ቃጠሎም የተወሰነ ቦታ መላጣ ሆኖ ሊቀር ይቺላል:: 🔹 አዋቂዎች ላይ ደሞ ዋናው መንስኤ በተፈጥሮ የተለያዩ በሽታዎችን የሚከላከልው የሰዉነት በሽታ መከላከያ ስርዓት(Immune system)ሴሎች የሰውነት ፀጉርን በሚያጠቁበት ጊዜ ላሽ (Alopecia areata) ይከሰታል:: 🔹 ላሽ እንደ ሥኳር በሽታ፤ ለምጽ ፤ እንቅርት ጋር መጠነኛ ተያያዥነት አለዉ:: 🔹 ከምግብ ቫይታሚን እጥረት ጋር ምንም አይገናኝም 🔹 በዘር ሊሄድ ይቺላል እስከ 20 የሚደርሱ ሰዎች ተመሳሳይ ችግር በቤተሰባቸዉ (በዘር) ሊታይ ይከሰታል ⏩ #የላሽ በሽታ አይነቶች 🔹 በሽታዉ በተለያየ የክብደት ደረጃ ይከሰታል፤ ከአነስተኛ የራስ ቅል ፀጉር መመለጥ(Alopecia areata ) እስከ ሙሉ የራስ ቅል ፀጉር መመለጥ (Alopecia Totalis) ከዚያም በከፋ መልኩ በሁሉም የሰዉነት ክፍሎች የሚገኝ ጸጉር መመለጥ (Alopecia Universalis) 🔹 በአብዛኛዉ ጊዜ በጥቂት ወራት አንዳንዴም በአመታት ጊዜ ዉስጥ ፀጉር እንደገና ሊበቅል ይችላል ፤ ነገር ግን ዳግም የመብቀል እድል በተከሰተዉ ምልጠት መጠን ይወሰናል ፤ መጠኑ አነስተኛ የሆነ ላሽ በአንድ አመት ዉስጥ ሙሉ ለሙሉ የመብቀል እድል ከፍተኛ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆን የፀጉር መመለጥ መልሶ የመብቀል እድሉ አናሳ ነዉ፡፡ ዳግም የሚበቅለዉ ፀጉር ነጭ ሊሆን ይችላል፡፡ ⏩ #አጋላጭ #ሁኔታዎች #ምንድናቸው? 🔹ጭንቀት 🔹የቆዳ አለርጂ 🔹ለምጽ 🔹በቤተሰብ ይህ ችግር ካለ ⏩ #በቤት #ውስጥ #ሊደረግ #የሚችል #መፍትሄዎች 🔹የቀይ ሽንኩርት ውሀ መቀባት 🔹የአረንጓዴ ሻይ ቅጠል ዱቄቱን መቀባት 🔹የሮዝማሪ ዘይት መቀባት 🔹ማር መቀባት 🔹የኮኮናት ዘይት መቀባት ⏩ #ላሽ በህክምና ይድናል? 🔹 ላሽ ሙሉ በሙሉ ፈዉስ የለዉም፤ መጠነኛ ላሽ ካለባቸዉ 5 ሰዎች ዉስጥ 4ቱ በአንድ አመት ጊዜ ዉስጥ ያለምንም ህክምና ፀጉራቸዉ ሙሉ በሙሉ ሊበቅል ይችላል፡፡ 🔹 ነገር ግን ከመነሻዉ ሰፋ ያለ የፀጉር መመለጥ ያጋጠማቸዉ ሰዎች ዳግም የመብቀል እድል ሰፊ አይደለም፡፡ 👉👉#ይህን እና ተያያዥ የሆኑ የጤና ጉዳዮች ላይ ያሎትን ጥያቄዎች ለማቅረብ ወደ 8809 ይደውሉ ከባለሙያ ጋር በቀጥታ በመገናኘት ይመካከሩ!! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ! (#በጤና #ባለሙያ #ማክዳ)
Nov 23, 2021Tnx betam amsgnalew bro
Nov 23, 2021Nech shnkurt fechtek bewha adrgek botaw lay hule tekebaw
Nov 23, 2021በ ዳይመንድ ፈግፍገው እና በ red ናይል ባህር ውስጥ ከዘፈዘፍከው በኋላ ኤቨረስት ተራራ ላይ ወተህ አይነ ምድርህን ተጸዳዳ ከዛ ይጠፋልሀል
Nov 23, 2021Ashofe eko adelm yalko 😏😏
Nov 23, 2021