ሰላም!!! እሄዉላቹህ እኔ በተፈጥሮየ በጣም አፋራም ነኝ።በተለይ ሴት ሳይ በቃ በጣም ነዉ ምጨነቀዉ ሴት ሲያወራኝ ማወራዉ ይጠፋብኛል።ሴቶችን መቅረብ በጣም ነዉ ምፈራዉ። በቃ ከሴት ልጅ ጋር የተቀራረበ ግንኙነት እንዲኖረኝ አልፈልግም ምክንያቱም በጣም ስለምፈራ ነዉ ከ elementary up to university ከማንም ሴት ጋር ተቀራርቤ አዉርቼ አላቅም።ግን ደሞ ተቀራርቤ ማዉራት እፈልግ ነበር።pls መፍትሄ ይሆናል ምትሉትን ሀሳብ አካፍሉኝ እስኪ
Nov 18, 2021መጀመሪያ ራስህን አስተሳሰብህን መለወጥ አለብህ እነሱም እንዳንተው ናቸውና ምንም የሚያስፈራ ነገር የለውም ልክ ጀለሶችህ ጋ እንደምትሆነው እነሱም ጋ መሆን ነው ለመግባባት ለመጫወት ሞክር ጊዜ ይፈልጋል እና በርታ...
Nov 20, 2021