ጥያቄ 1. ዋቃ ማነው አቴቴ ማናት ? 2. አባ ገዳ ማነው ሃደ ስንቄ ማናት ? 3. ዋቄፈና ምንድነው ? 4. ኢሬቻ የባእድ አምልኮ ነው ወይንስ አይደለም 5. ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ክርስቶስ የባህርይ አምላክና ፈራጅ ነው ስትል ፕሮቴስታን የለም አማላጅ ነው ትላለች(አላማዬ ይክን ማብራራት ስላልሆነ አልፈዋለው) ሙስሊም በአላህ ያምናል ጣኦት አምላኪውም እንደዛው የራሱ ፈጣሪ የሚለው አካል አለ ሁሉም በአምላክ ላይ ያላቸው እምነት እና እውነት ሲለያይ በአንድ ሰይጣን መኖር ግን ይስማማሉ። ( #ጥያቄዬ የሁሉም እምነት ተከታይ የሆነ የሚገኝበት ኢሬቻ በአል ላይ የሚመሰገነው የትኛው አምላክ ነው ? ) በጨዋነት ስለምትመልሱልኝ ከልብ አመሰግናለው።
Nov 17, 2021ሐዋርያው ጳውሎስ በገላትያ በመጀመሪያው ምእራፍ ላይ ለገላትያ ሰዎች እርሱ እንኳን ቢሆን ሌላ ወንጌልን ቢሰብክላቸው የተረገመ እንዲሆን በራሱ ላይ መስክሮአል ። የሰማይ መልአክ እንኳን ቢሆን። አንዳንድ ነገሮች በእግዚአብሔር ስም እንኳን ቢደረጉ መጽሀፍ ቅዱሳዊ መሰረት ከሌለው ራስን ወይም ሌላ ነገርን ማምለክ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። ለእውነተኛው አምላክ የጌታ ሐዋርያት እንዴት ነበር ምስጋናን ያቀርቡ የነበረው ? ወይስ መጽሀፍ ቅዱስ ለአምላካችን እንዴት ምስጋናን መስዋእት ማድረግ እንዳለብን ያስተምረናል ? መጽሀፍ ቅዱስን አለማወቃችን ለብዙ ስህተት ነገሮች ያጋልጡናል። ስለዚህ በዚህ አይነት በአል ላይ ዳግም የተወለደ ክርስቲያን ድርሻ ሊኖረው አይገባም ። በፍጹም ።
Nov 18, 2021